በኢትዮጵያ በተቀናጀ መንገድ የሰብኣዊ እርዳታዎችን ለማድረግ የሚያስችል ጥምረት ይፋ ሆነ፡፡
#fastmereja I 20 ሀገር በቀል ድርጅቶች የመሰረቱት The Consortium of Humanitarian Actors for National Growth and Empowerment (CHANGE) የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው ጥምረቱ ይፋዊ የምስረታ መርሃ ግብሩን በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡
እነደዚህ ያለ ጥምረት ሉዓላዊነትን ባከበረ መንገድ የሰብኣዊ እርዳታን ለመከወን ከፍተኛ ሚና አለው ያሉት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራሁ ተክለማርያም ጥገኝነትን የሚቀንስና ዘላቂ የሆነ መፍትሔን ለማምጣት የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
መንግስት ከሚያከናውናቸው ተግባራት ጋር በቅንጅት ለመጓዝ እንደሚረዳ በመግለፅም እንደ ስያሜው ሁሉ ለውጥ የሚያመጣ ጥምረት መሆን እንደሚገባውም ተናግረዋል፡፡
የጥምረቱ ሊቀመንበር ዶ/ር አንበሱ ቶላ በበኩላቸው ሀገር በቀል በሆኑ የጋራ መፍትሔዎችና የአመራር ስልት ዘላቂ የሆነ ውጤትን ለማምጣትና የመንግስትን የለውጥ ጉዞ ስራዎች ለመደገፍ የሚያስችል ጥምረት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መንግስት ሀገር በቀል ድርጅቶች ስራቸውን በአግባቡ የሚያከናውኑበት አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠሩን የተናገሩት ሊቀመንበሩ ጥምረቱ የሰብኣዊ እርዳታን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ይበልጥ በአግባቡ ለማድረስ የሚያስችል መደላድል ይፈጥራልም ብለዋል፡፡
በጥምረቱ ውስጥ የተካተቱት ሀገር በቀል ድርጅቶች በዘርፉ ለዓመታት የካበተ ልምድ ያላቸው ሲሆን ተፈናቃዮችን ማቋቋም ጨምሮ በእናቶችና ህፃናት እንዲሁም በኤች አይቪ መከላከል ዙርያ የሚሰሩ ናቸው፡፡

11 months ago