የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ትምህር በአማራ እና ትግራይ ክልል እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች ዙሪያ ማስተካከያ እንዲደረጉ ጥሪ አቅረበ
የኢትዮጵያ እስልምና ምክር ቤት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከሙስሊሙ መሪ ተቋም ጋር ሳይወያይ፣ ሙስሊም ተማሪዎች በግዳጅ ግዕዝ ቋንቋ እንዲማሩ ውሳኔ ማሳለፉን ተችቷል።
የክልሉ ውሳኔ በፍጹም ተቀባይነት የለውም ያለው ምክር ቤቱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ በውሳኔው ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወስድም ጠይቋል።
የትምህርት ቢሮው ውሳኔ የሙስሊሙን ማኅበረሰብ እና የእስልምና ተቋማትን ባገለለ መልኩ የተተላለፈ ነው ሲልም በመግለጫው ላይ ጠቅሷል።
ውሳኔው ክልሉ የገጠሙትን ውስብስብ ችግሮች ይበለጥ ያወሳስባልም ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም በትግራይ ክልል የሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ሙስሊም ተማሪዎችን በኢስላማዊ አለባበሳቸው ምክንያት ከሁለት ዓመታት በላይ ከትምህርት ገበታ ሲያግዱ፣ ትምህርት ሚንስቴር ተማሪዎቹ ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ ምንም ዓይነት ጥረት አለማድረጉ እንዳሳዘነውም አስታውቋል።
ኢስላማዊ አልባሳትን ለብሶ መማር ሕገመንግስታዊና ኃይማኖታዊ መብት መሆኑን የገለጸው ምክር ቤቱ ትምህርት ሚንስቴርና አንዳንድ የትምህርት ተቋማት ሙስሊሞችን በኢስላማዊ አለባበሳቸው ሳቢያ ከትምህርት የማፈናቀል ድርጊቶችን ባስቸኳይ ሊያቆሙ ይገባል ሲል ጠይቋል።
ምክር ቤቱ አክሎም በሁለቱ ክልሎች ላጋጠሙ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ የሚያፈላልግ ኮሚቴ እንዳቋቋመ አስታውቋል።

7 months ago