Logo
Getu Temesgen
ማርበርግ ቫይረስ

1) በሽታው ምንድን ነው?
#የቫይረሱ አይነት: ማርበርግ ቫይረስ የፋይሎቫይረስ (Filoviridae) ቤተሰብ አባል ሲሆን ይህም ኢቦላ ቫይረስ የሚገኝበት ቤተሰብ ነው። ለዚህም ነው ሁለቱም በሽታዎች ተመሳሳይ የሕመም ምልክቶች እና የሞት መጠን ያላቸው።
#ክብደት : በሽታው ከባድ እና ከፍተኛ የሞት መጠን ያለው ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ በተከሰቱ ወረርሽኞች በበሽታው ከተያዙት ውስጥ እስከ 88% የሚደርስ ሰዎች ሞተዋል (እንደ ወረርሽኙ ሁኔታ ሊለያይ ይችላል)። #ታሪክ : በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ በ1967 ዓ.ም በጀርመን ማርበርግ እና በፍራንክፈርት እንዲሁም በሰርቢያ ቤልግሬድ ከተሞች ተከስቷል። ቫይረሱ የመጣው ከዩጋንዳ በመጡ የላብራቶሪ ምርምር ዝንጀሮዎች አማካኝነት ነው ይባላል።

2) ስርጭት (በሽታው እንዴት ይተላለፋል?)
+++ ዋናው #ምንጭ : የማርበርግ ቫይረስ ተሸካሚዎች ፍራፍሬ ላይ የሚያዘወትሩ የሌሊት ወፎች (Rousettus bats) ናቸው። ሰዎች በቫይረሱ ሊያዙ የሚችሉት በእነዚህ የሌሊት ወፎች ባሉበት ዋሻዎች ወይም ማዕድናት ውስጥ በመገኘት ነው።

+++ ከሰው ወደ ሰው የሚኖረው #ስርጭት : ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በበሽታው የተያዘ ሰው ወይም እንስሳት በሚወጡ ፈሳሾች (ደም፣ ምራቅ፣ ማስታወክ፣ ሰገራ፣ ሽንት፣ የዘር ፈሳሽ እና ሌሎች) ጋር በቀጥታ በመገናኘት ነው።
3) #ምልክቶች
የበሽታው ምልክቶች በአብዛኛው ከ2 እስከ 21 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ይታያሉ።

የሚከተሉትን እንመልከት #የመጀመሪያ ደረጃ ላይ : ከፍተኛ ትኩሳት፣ ከባድ ራስ ምታት፣ ከባድ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመም፣ ድካም ስሜት። #ሁለተኛ ደረጃ (ከጥቂት ቀናት በኋላ): ከባድ ተቅማጥ፣ የሆድ ቁርጠት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ የደረት እና የጉሮሮ ህመም። #የከፋ ደረጃ (ከ5-7 ቀናት በኋላ) ከባድ የደም መፍሰስ (ከአፍንጫ፣ ከድድ፣ ከዓይን እና የቆዳ ስር)፣ የጉበት እና የኩላሊት ድካም፣ የንቃተ ህሊና መሳት፣ የብዝሃ-አካል ስራ መቆም (Multi-organ failure) እና ሞት። ከዚህ በተጨማሪ የዓይን መቅላት፣ የቆዳ ሽፍታ (በተለይ በደረት፣ ጀርባና ሆድ አካባቢ)።

4)የሚሰጠው ህክምና እና መከላከያ መንገዶች #ፈውስ : ለጊዜው ቫይረሱን የሚያጠፋ የተረጋገጠ መድኃኒት ወይም ክትባት የለም። #ህክምና : የሚሰጠው ህክምና ምልክቶችን ለማስታገስ (Supportive Care) ነው። #ፈሳሽ መተካት (IV fluids): በከፍተኛ ተቅማጥ እና ማስታወክ የጠፋውን ፈሳሽ መሙላት ነው። #የደም መፍሰስ ቁጥጥር: የደም ግፊትን ማረጋጋት እና የደም መርጋት መከላከል/ማከም። #የተጎዱትን የአካል ክፍሎች (ኩላሊት፣ ጉበት) ድጋፍ መስጠት።

በጣም #አስፈላጊው ነጥብ
-) የግል መከላከያ ቁሳቁስ (PPE): የጤና ባለሙያዎች የታመሙ ሰዎችን ሲያክሙ ጓንት፣ ጋውን፣ ጭንብል እና የዓይን መከላከያ የግድ መጠቀም አለባቸው።
_) ንጽህና: እጅን በአግባቡ በሳሙና መታጠብ፣ በተለይ የታመመ ሰው የነካን ወይም የጎበኘን ከሆነ።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ
1) የዓለም ጤና ድርጅት (World Health Organization - WHO): Marburg Virus Disease (MVD)

2) የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከላት (Centers for Disease Control and Prevention - CDC : Marburg Hemorrhagic Fever (Marburg HF)

ባምላኩ አበባው
ፕሮፌሽናል ነርስ እና የማህበረሰብ ጤና ባለሞያ
ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከል

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.