Logo
Getu Temesgen
የልጅነት እርግዝናን ማስቆም እንዳልተቻለ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
#ethiopia | የልጅነት እርግዝና ሴቶችን ለተለያዩ ተያያዥ የጤና ችግሮች ከማጋለጥ በተጨማሪ ያለ ዕድሜያቸው ሲያረግዙ ከትምህርት ገበታቸው ማቋረጥና ለሌሎችም ማህበራዊ ህይወታቸዉ መናጋት ምክንያት ነዉ።

በ2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእርግዝና ምርመራ ከተደረገላቸው 11ሺህ 767 አፍላ ወጣቶች ዉስጥ 1ሺህ 843 ሴቶች ለልጅነት እሮግዝና መጋለጣቸውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የቤተሰብ ዕቅድ ፣የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች የጤና ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አብረሀም ከብስራት ሬዳዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልፀዋል ።

ይህም የልጅነት እርግዝናን ለመቀነስ የሚሰሩ ስራዎች መጠናከር እንዳለባቸው አመላካች ናቸዉ ያሉት አስተባባሪው የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ጤና አገልግሎትን ለወጣቶች በማመቻቸት እንዲሁም ከመደበኛ የስራ ሰዓት ዉጪ ሰዓት በመመደብ የሚያዘወትሩባቸዉን ስፍራዎች በመለየት መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ያሳያል ብለዋል ።

ከባለድርሻ አካላት በተለይም ከትምህርት ቤቶች ፣ወጣቶችና ስፖርት ፣ሴቶችና ህፃናት እንዲሁም ከሀይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት አለብን ሲሉ አቶ አብረሀም ለጣቢያችን ተናግረዋል ።#dagu

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.