Logo
Getu Temesgen
የ12 ግለሰቦች አፅም ያረፈበትን ቦታ በማረስ ጫት የተከለው በ3 ዓመት እስራት ተቀጣ
#ethiopia | በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጐሮ ሙጢ ወረዳ፣ ወልተኢ ጃለላ ቀበሌ ውስጥ የአስራ ሁለት ግለሰቦች አፅም በክብር ያረፈበትን ቦታ በማረስ ጫት የተከለው ግለሠብ, በእስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን የወረዳው አቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

ሕግ ፅህፈት ቤቱ እንደገለፀው፤ ተከሳሽ ከድር አማን የተባለው ግለሰብ ለመካነ መቃብር የተከለለ ቦታ በመግባትና በማረስ ጫት ተክሏል፡፡

ተከሣሹ ሚያዝያ 22 ቀን 2017 ዓም ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጐሮ ሙጢ ወረዳ፣ ወልተአ ጃለላ በተባለ ስፍራ፣ የሙታን አፅም የክብር ማሣረፊያ መካነ መቃብር ውስጥ በመግባት፣ የአስራ ሁለት ሠዎች የመቃብር ቦታን በማረስ ጫት የተከለ በመሆኑ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ ሲጣራበት እንደነበረ ተገልጧል።

በአቃቤ ሕግ የተመሠረተውን ክስ የተመለከተው የጐሮ ሙጢ ወረዳ ፍርድ ቤት፣ ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት፣ ተከሣሽ ከድር አማን በተመሠረተበት ክስ ሙሉ በሙሉ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በሦስት ዓመት እስራትና በአንድ ሺህ ብር መቀጮ እንዲቀጣ የተወሠነበት መሆኑን የአቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤቱን ጠቅሶ ብስራት ዘግቧል።

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.