Logo
Getu Temesgen
በአስቸኳይ የጉበት ንቅለ ተከላ ያስፈልገዋል!

ወዳጆቼ ሼር አድርጉለት !
#ethiopia | ይህ ወጣት መልከመልካም ወንድማችን ማሩ አላምረው ይባላል፤ የባህርዳር ከተማ ዐ/ህግ ነው።በድንገት በመታመሙ ምክንያት በአስቸኳይ የጉበት ንቅለ ተከላ ያስፈልገዋል ተብሏል።

ስለ ልጁ ሙሉ መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ሥሜ ማሩ አላምረው እባላለሁ። የተማርሁት መራዊ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን ከዛም ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2006ዓ.ም በሕግ ተመርቂያለሁ። በአሁኑ ጊዜ በባህር ዳር ከዛ በፊት ደግሞ በቡሬ ወረዳ በዐቃቤ ሕግነት ሳገለግል ቆይቻለሁ።

ተወልጄ ካደግሁበት መራዊ ከተማ ድረስ የ7 ሠዓት የእግር ጉዞ በእየሳምንቱ እየተመላለስሁ ስማር የወደፊቱን የተሻለ ሕይወት ሰንቄ ነበር። እንደ ማንኛውም የገጠር ልጅ ለምስኪን ቤተሰቦቼም እደርስላቸዋለሁ የሚል ተስፋ ነበረኝ። ስፖርት መስራት ከመውደዴም የተነሳ በቴኳንዶ እስከ ጥቁር ቀበቶ ድረስ ደርሼ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቤ ሽልማቶችንም አግኝቻለሁ። በአጠቃላይ ለሕይወት አወንታዊ ግምት ነበረኝ።

ይሁን እንጅ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለሁ የጤና እክል ገጠመኝ። ሐኪም ቤት ስመረመር የጉበት በሽታ (Hepatitis B )እንዳለብኝ ተነገረኝ። በቀላሉ በመዳኅኒት ይድናል የሚል እምነት ነበረኝ። ነገር ግን ከማስታገሻ በዘለለ በመዳኅኒት የማይድን መሆኑን ሐኪሞች አረዱኝ።

እንደገለፅሁላችሁ እዚህ ላይ ተዘርዝሮ የማያልቅ ዋጋ ለከፈሉልኝ ገበሬ ቤተሰቦቼ ስል እንዲሁም ይሻለኛል ከሚል እምነት ሕመሜን ዋጥ አርጌ ትምህርቴን በርትቼ በመማር በመልካም ውጤት ከዩኒቨርሲቲ ተመረቅሁ።

የምወዳት እናቴ እና ዘመዶቼ የነገውን የተሻለ ሕይወቴን እያሰቡ በደስታ ከገጠር ተጉዘው አስመረቁኝ። እኔ ግን ሞት እንደሚጠብቀኝ እያሰብሁ ልቤ በሐዘን ይደማ ነበር። ለእኔ አይደለም የማስበው እኔን እዚህ ለማድረስ የለፉትን ዘመዶቼን፣በአናታቸው እህል ተሸክመው 7 ሠዓት እየተጓዙ ያስተማሩኝ ቤተሰቦቼን ሳስብ ሐዘኔን የከፋ ያደርግብኛል።

ሚስጢሬን በሆዴ ይዤ ለማንም ሳልተነፍስ እኖር ጀመር። ነገር ግን የጤናዬ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጣ። ሐኪሜ ጉበቴ በጣም እየተጎዳ ስለሆነ ያሉኝን አማራጮች ሁሉ እንድጠቀም ይመክረኛል። የጉበት ንቅለ-ተከላ (Liver Transplant) ካላደረግሁኝ በሕይወት መኖር የምችለው አጭር ጊዜ ብቻ መሆኑን ከነገሩኝ ዓመታት ተቆጠሩ። የሚከታተለኝ ሐኪም 'በዚህ ወጣትነት እድሜህ መሞት የለብህም፣ማድረግ የምትችለው ነገር ካለ ሞክር' አለኝ።

ይሁን እንጅ ሕክምናው የሚሰጠው ከአገር ውጭ ብቻ ነው። እኔ ደግሞ የኢኮኖሚ አቅሜ ይሔን ማድረግ እንደማያስችለኝ አውቃለሁ። ዝም ብዬ እግዚአብሔር እስካኖረኝ ለመኖር አስባለሁ። በሌላ ልቤ ደግሞ ሁኔታዬን የነገርኋቸው ወንድሞቼ ለምን የሚቻለውን አንሞክርም ይሉኛል። እኔም በሀሳባቸው ተስማምሁ።

ሕንድ አገር ለሚደረገው ሕክምና የሚያስፈልገኝ 5 ሚልዮን ብር በላይ ነው ተባልሁ። ከደሀ ቤተሰቦቼ እንዲሁም ከቅርብ ዘመዶቼ የተወሰነ ገንዘብ ለመሰብሰብ ብሞክርም ከሚያስፈልገኝ ወጭ አንፃር በጣም ትንሽ በመሆኑ ተስፋ ያስቆርጠኛል። ከተመረቅሁ ጀምሮ ስራ ላይ ብሆንም ከኑሮዬ ተርፎ ለከፍተኛ ሕክምና የሚሆን ገንዘብ ገና አላፈራሁም። ያለኝንም በእዬሦስት ወሩ ለሕክምና በመመላለስ ከ 2007 ዓ.ም ጀምሮ ተጠቅሜበታለሁ። አሁንም ሕመሙ እየጠናብኝ ስለመጣ እና ሥራ መስራትም ስላልቻልሁ ከህክምና ወጪው ጋር ተደማምሮ ከአቅሜ በላይ ሆኗል።

በሀይስኩልም፣በዩኒቨርሲቲም ፣ በአካባቢም የምታውቁኝ ፣ በአካል የማታውቁኝ ሕመሜን የምትገነዘቡ ሰዎች እባካችሁ የምትችሉትን እርዱኝ።

https://gofund.me/de7259b1...

የንግድ ባንክ አካውንት፡ 1000128144319
የአካውንቱ ባለቤት ስም: ማሩ አላምረው
አቢሲኒያ ባንክ፡ 53636527 ማሪ አላምረው

©️ John Abere

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.