የኖቤል ተሸላሚው ሳይንቲስት ጄምስ ዋትሰን በ87 አመታቸው አረፉ
ቢቢሲ እንደዘገበው የዋትሰንን ሞት ያረጋገጠው ለዓመታት የሰሩበት እና ምርምር ያደረጉበት ኮልድ ስፕሪንግ ሃርቦር ላቦራቶሪ ነው።
ጄምስ ዋትሰን ከብሪቲሽ ሳይንቲስት ጋር በመሆን በ1953 ዓ.ም. የዲ ኤን ኤን ድርብ-ጥምዝ መዋቅር ለይተው አውቀው ነበር፤ ይህም የሞለኪዩላር ባዮሎጂ ፈጣን ዕድገት እንዲኖር መንገዱን ከፍቷል።
ይህ ግኝት ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ታላላቅ ሳይንሳዊ ስኬቶች አንዱ ተደርጎ ይወሰዳል።
ሆኖም ግን ዝናቸው በዘር እና በፆታ ላይ በተሰጡ አወዛጋቢ አስተያየቶች ምክንያት በእጅጉ ተጎድቷል።
በአንድ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ በነጮች እና በጥቁሮች መካከል ባለው አማካይ የአይ ኪው ልዩነት ምክንት ጂኖች ወይም የዘረመል ምክንያቶች እንደሆኑ ተናግረው ነበር።
ዋትሰን የዲ ኤን ኤን ድርብ-ጥምዝ መዋቅር በማግኘታቸው የ1962 ዓ.ም. የኖቤል ሽልማትን ከሞሪስ ዊልኪንስ እና ከክሪክ ጋር ተካፍለዋል።
በወቅቱ "የህይወትን ምስጢር አግኝተናል" ብለው ነበር።
በኋላም በዘር ላይ በሰጡት አስተያየት ምክንያት ከሳይንሳዊው ማህበረሰብ እንደራቁ ተሰምቷቸው እንደነበር ተናግረዋል።

11 months ago