Logo
SeledaPost
በይርጋጨፌ የአረቄ ንግድ ቢከለከልም 65 ጀሪካን አረቄ በድብቅ ሲጓጓዝ በቁጥጥር ስር ዋለ

በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌከተማ ፖሊስ የተከለከለ 65 ጀሪካን የአረቄ መጠጥ በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል ።

በቁጥጥር ስር የዋለዉ 65 ጀሪካን አረቄ ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም መነሻዉን ከነገሌ አድርጎ በይርጋጨፌ ከተማ ዉስጥ ጨለማን ተገን በማድረግ ለአረቄ ቤቶች እየተራገፈ እያለ በዕለቱ ተረኛ ሮንድ ፖሊሶች ከእነ መኪናዉ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የይርጋጨፌ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ፍቃዱ ሲሳይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

አረቄ ባህላዊ መጠጥ ተብሎ ቢነገድም ከስሪቱ አንፃር የተለያዩ ባዕድ ነገሮች እየተጨመረበት በዜጎች ላይ ከፍተኛ የጤና እክል እየፈጠረ በመሆኑ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ሰፊ ዉይይት ተደርጎበት በይርጋጨፌ ከተማ የአረቄ ንግድ ክልከላ መደረጉ ይታወሳል ።

በእጃቸዉ ላይ ያለዉን ጨርሰዉ እንዲያቆሙ በተሰጣቸዉ የቀን ገደብ መሠረት አብዛኛዎቹ አረቄ ቤቶች ይህን ተግባራዊ ቢያደርጉትም በድብቅ የሚሸጡ ስለመኖራቸዉ በቁጥጥር ስር የዋለዉ አረቄ ማሳያ ነዉ ተብሏል ።አዛዡ ከድርጊታቸው በማይቆጠቡ አካላት አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል ።

Dagu

Addis_News
Addis_News
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.