Logo
FIDEL POST NEWS
ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የደረሰበት ኪሳራ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ59 በመቶ ቀንሷል አለ

የኬንያው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያ የኢትዮጵያ ኦፕሬሽን ኪሳራው በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ እና በሀገር ውስጥ ገበያ ያለው የተረጋጋ ዕድገት ለትርፉ መጨመር መነሻ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ኩባንያው እስከ መስከረም ወር ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ 65.2 ቢሊዮን የኬንያ ሺሊንግ (506 ሚሊዮን ዶላር) የሥራ ትርፍ አስመዝግቧል። በኢትዮጵያ የደረሰበት ኪሳራ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ59 በመቶ ቀንሷል።

የቡድን የአገልግሎት ገቢም ጤናማ ዕድገት አሳይቶ 199.9 ቢሊዮን ሺሊንግ (1.5 ቢሊዮን ዶላር) ደርሷል። ለዚህ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከተው የሳፋሪኮም የሞባይል የፋይናንስ አገልግሎት የሆነው ኤም-ፔሳ ሲሆን ገቢውም 88.1 ቢሊዮን ሺሊንግ (681.9 ሚሊዮን ዶላር) ሆኖ ተመዝግቧል።

በኢትዮጵያ የታየው የተሻለ አፈጻጸም ሳፋሪኮም ለወደፊት በሀገሪቱ ተደራሽነቱን ለማስፋት እና ለውድድር ክፍት በተደረገው ገበያ ላይ ተስፋ እንዲጥል አዎንታዊ እርምጃ መሆኑ ተዘግቧል።
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.