የ12 ዓመቷን የእንጀራ ልጃቸዉ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸሙት የ75 ዓመቱ አዛዉንት በእስራት ተቀጡ
የወንጀል ድርጊቱ በጅማ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ጅሬን ቀበሌ መፈጸሙን ፖሊስ አስታዉቋል። የጅማ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ፖሊስ ፅህፈት ቤት የሴቶች እና ሕፃናት የወንጀል ምርመራ መርማሪ ሣጅን ሲፍቱ በላይ እንደገለፁት ተከሣሽ ናስር አባ ቡልጉ የተባሉት የ75 ዓመት አዛዉንት ድርጊቱን በ12 ዓመቷ የእንጀራ ልጃቸዉ ላይ ፈጽመዋል፡፡
መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓም ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ ጥቃቱን ሊፈጹሙ የቻሉት የታዳጊዋ እናት ጎረቤት ለቅሶ ለማስተዛዘን ባመሹበት ወቅት በነዉ።ወላጅ እናት ከለቅሶ ቤት ሲመለሱ ታዳጊዋ ልጅም በደረሠበት ጥቃት ደም በደም ሆና በመመልከታቸው ወዲያው ጎረቤት ጠርተው ጉዳዩን ለፖሊስ አሳዉቀዋል፡፡
ታዳጊዋ ጥቃቱን ማን እንፈጸመባት ለፖሊስ በሰጠችው መረጃ መሠረት ተከሳሽ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡ በተጨማሪም በሕክምና ምርመራ ተደርጎላት ውጤቱን ፖሊስ በማያያዝ መዝገቡን ለአቃቤ ሕግ ልኳል።ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ የተመለከተው አቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ በወንጀል ሕግ ቁጥር 627 መሠረት ክስ መስርቷል።
በአቃቤ ሕግ የተመሠረተውን ክስ የተመለከተው የጅማ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ናስር አባ ቡልጉ ጥፋተኛ በማለት በ18 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል።Via : dagu
seledadotio

8 months ago