Logo
Getu Temesgen
ኑ !!! ጌትነትን እንየው ።
( ታላቁን የኪነ-ጥበብ ሰው እናመስግነው )
#ethiopia | ጸሐፊ ተውኔቱ ፣ ገጣሚው ፣ አዘጋጁ ፣ ተዋናዩ ፣ በሁሉ ተወዳጁ ጌትነት እንየው 68 መስቀል ተኩሷል ፤ 68 ክረምትና 68 በጋ አይቷል ፤ 68 እንቁጣጣሽ ፣ 68 ፋሲካ አክብሯል ። ከዚህ ውስጥ ደግሞ 43 ዓመት በጥበብ ላይ ነግሷል ። 43 ዓመት " ጌትነት ! ጌትነት ! " ተብሏል ። ሁሉ ወዳጁ ሁለገብ የኪነጥበብ ሰው ዘንድሮ 68ኛ ዓመት ልደቱ ነው ። ሁሉም ቀንና ሰዓት ከሌላው ቢለይም የዘንድሮው የታላቁ የኪነጥበብ ሰው የልደት በዓል ግን ከ67ቱ በተለየ ሁኔታ በምስጋና ሊከበር ነው ።

በተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ ፣ በአርቲስቱ የቅርብ ቤተሰቦች እና ወዳጆች በጋራ የተዘጋጀውን 68ኛ ዓመት የልደት በዓልና የ43 ዓመት የሙያ አገልግሎት ምክንያት በማድረግ የፊታችን ሰኞ ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሠዓት ላይ አርቲስቱን የማመስገን ልዩ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ተዘጋጅቷል።

እርስዎም በዕለቱ ተገኝተው ለተወዳጁ አርቲስት ያለዎትን አክብሮት እና ፍቅር እንዲገልጹ የክብር እንግዳችን ነዎት ።

በእለቱ የሚከናወኑ ፕሮግራሞች:-

1.ከቀኑ 11:00 ሠዓት ጀምሮ በርካታ የኪነ-ጥበብ ሰዎች በተገኙበት በፌደራል ፖሊስ ማርቺንግ ባንድ በመታጀብ ለዕለቱ የክብር እንግዶች ( ለእርስዎ ) እና ለታላቁ የጥበብ ሰው ጌትነት እንየው ልዩ የአቀባበል ሥነ-ስርዓት ይካሄዳል።

2.ታዋቂ ድምጻዊያን የሚሳተፉበት ልዩ የሙዚቃ ዝግጅት ይካሄዳል።

3.በአርቲስቱ ስም የተዘጋጀ ተውኔት ይቀርባል።

4.አርቲስት ጌትነት እንየው በድርሰት፣ በዝግጅት፣በትወና የተሳተፈባቸው ስራዎች በፎቶግራፍ መልክ ይቀርባሉ።

5.የተለያዩ የሙያ አጋሮቹ በሀገር ውስጥም በውጪም ያሉ ባለሙያዎች መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።

6.የተለያዩ ሰርፕራይዝ ፕሮግራሞች ይኖራሉ።

( የዚህ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ኢንተርፕራይዝ ተፈራ ወርቁ፣ የአርቲስቱ የቅርብ ወዳጀች እና ቤተሰቦቹ በጋራ በመሆን ነው። )

Via ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ
#share በማድረግ ለጌትነት እንየው ያለዎትን አጋርነት ያሳዩ ።

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.