Logo
Getu Temesgen
ኢትዮጵያ ተጋጣሚዋን አውቃለች !
#ethiopia | ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚረዳውና ሀገራችን የምታስተናግደው የሴካፋ ከ 17ዓመት በታች ውድድር የምድብ ድልድል ወጥቷል።

ይህንንም ተከትሎ ሀገራችን ኢትዮጵያ በምድብ አንድ

- ከሱማሊያ
- ኬኒያ
- ደቡብ ሱዳና እና
- ሩዋንዳ ጋር ተደልድላለች።

አስር ሀገራት በሚካፈሉበት ይህ ተጠባቂ ውድድር ከ ህዳር 6 እስከ ህዳር 23/2018 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ይደረጋል።

ውድድሩ አስር ሀገራት በሁለት ምድብ ተከፍለው በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እና በድሬዳዋ ስታዲየም ውድድራቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል።

የ ኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በትላንትናው ዕለት በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር እየተመሩ ይፋዊ ዝግጅታቸውን ለውድድሩ ጀምረዋል።
#ts #sport #gtmc

12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.