ጃምታራን ይተዋወቋት፡ የህንድ ዲጂታል ማጭበርበር ማዕከል የሆነችው ትንሽ ከተማ
በመጀመሪያ ሲታይ ጃምታራ ከተማ ከምስራቅ ህንድ አውራጃዎች የተለየች አትመስልም። ቀላል ቤቶች ከእርሻና ከጫካ ጎን ተሰልፈዋል። ነገር ግን ትልቁ የማጭበርበር ወይም የአታላይነት ጥበብ የሚወጣው ከዚች ከተማ ነው።
ባለፉት 15 ዓመታት ውስጥ፣ ይህ አውራጃ የሳይበር ወንጀል ምልክት ሆኗል። እዚያ ያሉት ወጣት ወንዶች ሞባይል ስልክ ብቻ ታጥቀው፣ የሰዎችን ገንዘብ ከባንክ ሂሳብ የማውጣት ችሎታ ያላቸው ሲሆን፣ ይህም ብዙ ጊዜ ባንክ የመዝረፍ ያህል ይቆጠራል።
በዘ ጋርዲያን እንደተዘገበው፣ ይህ ክስተት በህንድ ውስጥ ካለው ፈጣን ዲጂታላይዜሽን ጋር ጎን ለጎን ብቅ አለ። መንግሥት "ዲጂታል ህንድ" በማለት ቢፎክርም፣ አብዛኛው ዜጋ ግን ይህንን የሚያገናኘው ከጃምታራ ማጭበርበር ጋር ነው። ኔትፍሊክስ “Jamtara: Sabka Number Ayega” ማለትም “ለሁሉም ሰው ይደወላል” የሚል ተከታታይ ድራማ ሳይቀር አዘጋጅቷል።
እንደ ዘገባዎች ከሆነ፣ ከፈረንጆቹ 2015 ጀምሮ ከተለያዩ ክፍለ ሀገራት የመጡ ፖሊሶች በዚህ አካባቢ በተደጋጋሚ ምርመራ አድርገዋል።
ሆኖም እስራት የተለመደ ነገር ሆኗል። ቀለል ያሉ ቅጣቶች ደግሞ የማጭበርበር ንግዱ እንዲያድግ አስችለዋል።
ከወንጀለኞቹ አንዱ የሆነው ጂቱ፣ ገና በወጣትነት ዕድሜው ዋና አታላይ እንደነበር አምኗል። ሊታለሉ የሚችሉ ሰዎችን እንዴት መለየት እንዳለበት ከአለቆቹ ተምሯል። "እነዚያን ቁጥሮች በራስህ መደወል አትችልም" ብሏል።
በስልክ ጥሪ ላይ የተመሠረተው ማጭበርበር የሚጀምረው በቀላል ዘዴ ነው፡ የባንክ ሰራተኛ መስሎ በመቅረብ ለማረጋገጫ በሚል ሰበብ የተጎጂውን የግል መረጃ ይጠይቃል።
"የባንክ ማንነት ማረጋገጫ (KYC) ሂደቱን ለማጠናቀቅ፣ ወደ ሞባይል ስልክዎ የተላከ ባለ ስድስት አሃዝ ኮድ ማንበብ አለብዎት" ብሏል። ያ ኮድ ኦቲፒ ነው። ተጎጂው ኮዱን እንዳነበበ፣ ገንዘቡን ማስተላለፍ ይቻላል።
ሲታራም ማንዳል የዚህ ወንጀል አቅኚ እንደሆነ ይነገራል። እሱ አንድ ጊዜ በሙምባይ በሚገኝ የሞባይል ስልክ ካርድ መሙያ ሱቅ ውስጥ ይሠራ ነበር፣ በዚያም በመስመር ላይ እንዴት እንደሚሰርቅ አገኘ።
"የተጎጂውን ስልክ ወይም የባንክ ሂሳብ 'ሃክ' ማድረግ አያስፈልግም። እነሱ ፈቃደኛ ሆነው መዳረሻ ይሰጡዎታል፤ እርስዎ መዋሸት ብቻ ነው ያለብዎት" ብሏል። ማንዳል ከዛ በኋላ "ችሎታውን" በመንደሩ ውስጥ ለሚገኙ ወጣቶች አስተማረ። እና አሁን፣ ሳይበር-ቸር ወይም ዲጂታል ሌቦች በሚል በሰፊው የሚታወቅ አውታረ መረብ ብቅ ብሏል።

8 months ago