ሠዓሊ ቀፀላ ማርቆስ እና ሀንጋሪያዊው መምህር በግዕዝ ቋንቋ ላይ ያድረጉት አስገራሚ ታሪካዊ ክርክር
(ይትባረክ ዋለልኝ)
#ethiopia | ይህን አስገራሚ የታሪክ ማስታወሻ ፁሑፍ የላከልኝ ወዳጄ ደራሲ ዳንኤል ወርቁ ነው::እኔም ፁሑፉን አነበብኩት:: ሌላው ዓለም ስለ ግእዝ ቋንቋ ያለውን የላቀ ግምትና አስተያየት እና ግዕዝን ለሚያውቅ ሰው የሚሰጡትን ክብር ስመለከት እጅግ ገረመኝ:: አንብቤው እጅግ ስለወደድኩት ዳንኤልን ለፌስቡክ ወዳጆቼ እንዳጋራው ጠየኩት:: እርሱም ፈቀደልኝና
ርዕስ ሰጥቼው ይሄው ለወዳጆቼ አጋራሁት:: ስለ ፁሑፋ የተሰማችሁን አስተያየት አጋሩን ::ታሪኩን እንሆ!!
“አንድ ቀን አሉ ሰዓሊ ቀፀላ ማርቆስ” ያገኘኋቸው ተባባሪ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን የኢትዮጵያን ታሪክ በአስገራሚዎቹ ኢትዮጵያውያን ግለ ታሪክ ወስጥ እያፈላለገ በነበረ ጊዜ እንደ እድል ሆኖ ይዞኝ ቢሮአቸው ሄዶ ነው። ቀፀላ ማርቆስ ብዙ አስገራሚ ታሪካቸውን ለበቀለ ሲያጫውቱት አዳመጥኩ።
እና ሰሞኑን ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ስለ ግዕዝ እየተወያዩ ነው ሲሉ ስሰማ እኝህ ታላቅ ሰዓሊ በህይወታቸው ስለገጠማቸው አንድ አስደናቂ ቀን ያጫወቱን ታሪክ ትዝ አለኝ።
ባጭሩ የማስታውሰውን ብፅፈውስ ብዬ በዛውም የኛን የሚያስገርም ታሪክ ያላቸውን እኛ የት እንዳሉ የማናውቀውን ግን አለም ያከበራቸውን ታላቅ ሰዓሊ ስም ለማንሳት ስል ይህን አደረኩ። ተባባሪ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን አንድ ቀን ሙሉ ታሪካቸውን ያስነበብበን ይሆናል የሚል እምነት አለኝ።
ሀገሬን እና ሕዝቤን ከፍ ከፍ ያስደረኩበት አጋጣሚ
እና አንድ ቀን ብለው ነበር የጀመሩት ትዝታቸውን። ሰዓሊ ቀፀላ ማርቆስ የተማሩት ሀንጋሪ ነው። “እና አንድ ቀን አንድ የተከበረ ሀንጋሪያዊ መምህር፣ የጥበብን ታሪክ እያስተማረን በመሀሉ ከምድረ ገጽ ስለጠፉ ቋንቋዎች ከሚሶፕታምያ ተነስቶ መካከለኛው ምስራቅ አቋርጦ በግብፅ አድርጎ ምስሎችን እያሳየ ሲያስተምረን በመሀሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሳተመው፣
“ቅዱስ ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ” በግዕዝ ቋንቋ የተፃፈበት ምስል መጣ። ከዛ እኔ እጄን አወጣሁና ይህን ቋንቋ ማንበብ እችላለሁ አልኩ። ምምህሩን አሳቀው። ከዛም “አትቀልድ እንኳን አንተ ከአፍሪካ የመጣህ የእኛም ሀገር ድንቅ ሊቃውንት አይችሉትም አለኝ።
"አይ እኔ እችለዋለሁ” አልኩ። ተናደደ።
“አይ አትችለውም” አለኝ መልሶ። ከዛ ክርክር ውስጥ ገባን። በዚህ ጊዜ አብረውኝ የሚማሩ ፈረንጆች ቀደም ብለን የዱር እንስሳ መቆያ ስንጎበኝ አንዲት ጦጣ አይተን ሰለነበር። አይ ይሄው እንግዲህ ተነሳበት አክስቱ ናፍቃው ወደ እሷ መመለስ ፈልጎ ነው” እያሉ ሊያበሽቁኝ ሞከሩ። እኔ ግን “አውቀዋለሁ” ብዬ ድርቅ አልኩ። አስተማሪው የሃንጋሪ ፓርላማ አባልና ትልቅ ስልጣን ያለው ሰው ስለነበር ሊያባርረኝ የሚችል ሰው ነው። ከዛ በስላይድ ነበር የምናየው አቋረጠ። መብራት አበራ ና ውጣና ብላክ ቦርድ ላይ ፃፈው አለኝ። እኔም ቁም ፅህፈቷን አሳምሬ ፃፍኩ። ስጨርስ ሁሉም አጨበጨቡ። ግማሾቹም ደነገጡ። ይህን ትቸላለህ አንተ? እያሉ ጠየቁኝ። ከዛ መምህሩ ወረቀት አመጣና
“እንደገና እዚህ ላይ ፃፈው” አለኝ።
ሰማንያ የግዕዝ ሆሄያት ናቸው። ስጨረስ ወረቀቷን ይዞብኝ ሄደ። በጣም ተናዶ ስለነበር ፊቱ ሳምባ መሰለ። “እንዴት አንድ አፍሪካዊ በስኮላርሽፕ የመጣ ይህን አውቃሁ ይላል” ይል ነበር ደጋግሞ።
ከዛ ለነገ ከዚህ ዲፓርትመንት አነ እገሌን እነ እገሌን እንድተጠራ ብሎ ረዳት መምህሩን አዘዘው ና ሄደ። ንዴቱን ያዩ አብረን የምንማረው ጓደኞቼ ማታ እነሱም ለማመን ስላልቻሉ
“እንዴት አንተ በሙያው ጎበዝ ሆነህ አስተማሪውን ልታጭበረብር ትሞክራለህ። በል አሁን ልብስህን እጠብና ተዘጋጅ። ነገ አንጠልጥሎ ግብፅ ወስዶ ይጥልሃል።” አሉና ተሰናበቱኝ። ጭቅጭቁ ሰቢዛበኝ ራሴን ሁሉ አመመኝ። በማግስቱ ትልልቅ ምሁራን ተሰብስበው መጡ። የሚገርመው እና ያስደነቀኝ ነገር በማግስቱ መምህሩ እኔን መጠየቅ አልፈለገም። በደንምብ የቤት ስራውን ሰርቶ ሰለ ኢትዮጵያ አንብቦ ፅሁፌንም አጣርቶ ስለመጣ እኔ መናገር አላስፈለገኝም። እንዲያውም ስለ አድዋ የኢትዮጵያ ጀግኖች ታሪክ፣ ስለማይጨው ጦርነት፣ ስለ አምስት አመቱ የኢትዮጵያውያን ቆራጥ ተጋድሎ፣ ብዙ ሀገራትን እየጠቀሰ፣ እነሱ ሰጥ ለጥ በለው ሲገዙ ኢትዮጵያውያን ግን በባዶ እግራቸው ሳይታክቱ እንደተዋጉ በከፍተኛ ኩራትና አክብሮት ለተሰበሰቡት ነገራቸው። ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን በክብር አወደሰ። ኮራ አልኩ። ፈገግ ያደረገኝ ደግሞ ቁመታቸው ሁሉም አጭሮች ናቸው ልባቸው ነው ረጅም ሲል ነው። በዚህ አላቆመም።
ከዛሬ ጀምሮ እሱ ተማሪ ሳይሆን ተመራማሪ ነው። ለብቻው ክፍል እንዲሰጠው። የሚከፈለውም እንደ ተማሪ ሳይሆን እንደ ተመራማሪ እንዲሆን አለ ሁሉም ተሰማሙ። ከዛ ጓደኞቼ በጣም ያከብሩኝ ጀመር። “ለካ ሞኝ መስለህ እንዲህ አዋቂ ነህ” እያሉ ይንከባከቡኝ ጀመር። በጣም ኮራሁ። አንተ አንደኛ አመት ሳይሆን ከሁለተኛ አመት ነው መጀመር ያለብህ ተባለ።
ከዛ ደግሞ በቫቲካን የሚተዳደር የተርጎም የሚባል የካቶሊክ ሴንተር አለ። ቼኮዝላቫክያ እና በሃንጋሪ መካከል ዳኑብ ወንዝ አካባቢ የሚገኝ ነው። እዛ በግራኝ አህመድ ጊዜ ለቱርኮች የተሰጠ ስንክሳር አለ። ካቶሊኮቹ መስቀል ስላዬ ምናልባት የክርስቲያን መፅሀፍ ይሆናል ብለው ሙዝየም ውስጥ በክብር አስቀምጠውት ነበር።ትምህርት ቤት የሆነውን ሲሰሙ ወደ ገዳሙ ጋበዙኝ እና ስንክሳሩን አውጥተው ይህን ትችለዋለህ አሉኝ። አነበብኩላቸው ከዛ ዜማውንም ወጣሁት በጣም ተደሰቱ። ሀገሬን በክብር በማስጠራቴ በሕይወቴ የተደሰተኩበት ጊዜ ነበር።

7 months ago