Logo
Getu Temesgen
ኢትዮጵያ ተጋጣሚዋን ነገ ታውቃለች
#ethiopia | ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚረዳውና ሀገራችን የምታስተናግደው የሴካፋ ከ 17ዓመት በታች ውድድር በነገው ዕለት በዩጋንዳ የምድብ ድልድል ይውጣል።

አስር ሀገራት በሚካፈሉበት ይህ ተጠባቂ ውድድር ከ ህዳር 6 እስከ ህዳር 23/2018 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ይደረጋል።

ውድድሩ አስር ሀገራት በሁለት ምድብ ተከፍለው በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እና በድሬዳዋ ስታዲየም ውድድራቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል።

ተካፋይ ሀገራት እነማን ናቸው ?

- ኢትዮጵያ
- ዩጋንዳ
- ሱዳን
- ደቡብ ሱዳን
- ቡሩንዲ
- ታንዛኒያ
- ሩዋንዳ
- ሶማሊያ
- ኬንያ እና
- ጅቡቲ በውድድሩ የሚካፈሉ ቡድኖች ናቸው።

የ ኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በትላንትናው ዕለት በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር እየተመሩ ይፋዊ ዝግጅታቸውን ለውድድሩ ጀምረዋል።
#ts #sport #gtmc

12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.