ከእንግሊዝ የተባረረው ሃዱሽ ለሊት ኢትዮጵያ መግባቱ ተገለፀ::
በግብረ ስጋ ፍላጎት ወንጀል ተከሶ በእስር ላይ የነበረው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሃዱሽ ገብረሥላሴ ከባቱ፣ በእንግሊዝ (UK) የወህኒ ቤት አስተዳደር ስህተት ከተፈጠረ በኋላ፣ አሁን በይፋ ወደ ኢትዮጵያ መላኩ ተረጋገጠ።
ሃዱሽ ከባቱ በኤሰክስ ውስጥ የ14 ዓመት ታዳጊን እና ሌላ ሴትን ለመድፈር በመተናኳል በሴፕቴምበር 2025 ዓ.ም የ12 ወራት እስራት ተፈርዶበት ነበር።
ከእስር በኋላ ለስደት ዓላማ ወደ ኢሚግሬሽን ማቆያ (Immigration Detention) መዛወር ሲገባው፣ በHM Prison Chelmsford በተፈጸመ ከባድ የአስተዳደር ስህተት ምክንያት በድንገት ተለቀቀ።
ይህ ስህተት በመላው ዩኬ ብሔራዊ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፣ ወዲያውኑ ሰፊ ፍለጋ ተጀመረ።
ፖሊስም ከቀናቶች በኃላ ግለሰቡን በድጋሚ በቁጥጥር ስር አውሎ ለስደት ባለሥልጣናት ማስረከቡን አረጋግጧል።
ባለሥልጣናት አሁን ላይ ሃዱሽ ገብረሥላሴ ከባቱ ትላንትና ወደ ኢትዮጵያ መባረሩን ኢትዮጵያ መግባቱን አረጋግጠዋል፤ ይህም በስህተት መልቀቅ ዙሪያ የተፈጠረውን ውዝግብ አብቅቷል።
የዩኬ ባለሥልጣናት እንደዚህ ዓይነቱ ስህተት ዳግም እንዳይከሰት ለማድረግ ሙሉ ምርመራ በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
Via Gursha

8 months ago