Logo
YenetaTube
ትራምፕ በ2028 በሚደረገዉ ምርጫ ለምክትል ፕሬዝዳንትነት እንደማይወዳደሩ ገለጹ

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸዉ ለተጨማሪ አንድ ዙር በስልጣን ላይ እንዲቆዩ ቢፈልጉም እርሳቸዉ ግን ሃሳቡን ዉድቅ አድርገዉታል፡፡

በአሜሪካ ህገመንግስት መሰረት ማንም ሰዉ ለሶስተኛ ጊዜ በፕሬዝዳንትነት መመረጥ አይችልም፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ የሰጡት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህንን ለማድረግ ፍቃድ አለኝ ነገርግን አላደርገዉም፤ ሰዎችም ደስ የሚላቸዉ አይመስለኝም ፤ ትክክልም አይደለም ሲሉ መልሰዋል፡፡

ለሶስተኛ ዙር ስልጣን ሊወዳደሩ የሚችሉበት ዕድል አለ ወይ ተብለዉ የተጠየቁት ፕሬዝዳንቱ፤ ባደርገዉ ደስ ይለኛል፤ ያለኝ ቁጥራዊ መረጃዎችም በጣም ምርጥ ናቸዉ ብለዋል፡፡

ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ፤ ለስልጣን መወዳደር የሚችሉ የተሻሉ ሰዎች ናቸዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ የሆነ ቡድን መፍጠር ቢችሉ የሚያስቆማቸዉ ያለ አይመስለኝም፤ ይህንን በደንብ የማምንበት ጉዳይ ነዉ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ETHIO FM

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.