ኩላሊቱን ለ'አይፎን' የሸጠው ወጣት አሳዛኝ ዕጣ ፈንታ፡ የቅንጦት ፍላጎት ያስከተለው የሕይወት ውድመት
እ.ኤ.አ. በ2011 ዓ.ም. በቻይና አንሁይ ግዛት ይኖር የነበረ ዋንግ የተባለ ወጣት፣ አይፎን እና አይፓድ ለመግዛት ሲል ኩላሊቱን በሕገወጥ መንገድ መሸጡን ተከትሎ ዓለም አቀፍ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
በወቅቱ ገና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የነበረው ዋንግ፣ ለቁሳዊ ፍላጎት ሲል በከፋና ንጽህና በጎደለው ሁኔታ ውስጥ በተደረገለት ሕገወጥ ቀዶ ሕክምና ምክንያት ለሕይወት አስጊ የሆነ ኢንፌክሽን አጋጥሞት ነበር። ይህ ደግሞ በጊዜ ሂደት ቀሪው ኩላሊቱ ከጥቅም ውጪ እንዲሆን አድርጓል።
ወጣቱ ዋንግ በአሁኑ ጊዜ በኩላሊት ሥራ ማቆም (Kidney Failure) በሽታ ምክንያት በከፍተኛ የጤና ችግር እየተሰቃየ ይገኛል። ለመኖርም በየቀኑ በሚሰጠው የዳያሊሲስ ሕክምና ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ ሆኗል ነው የተባለው፡፡
ይህ አሳዛኝ ታሪክ ሰዎች የቁሳዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ምን ያህል ርቀት ሊሄዱ እንደሚችሉ እና እንዲህ ያሉ ውሳኔዎች የሚያስከትሉት መዘዝ ምን ያህል አስከፊና ሕይወት አጥፊ ሊሆን እንደሚችል የሚያሳይ ኃይለኛና አስተማሪ ማስጠንቀቂያ ሆኗል ነው የተባለው።
seledadotio

12 months ago