Logo
Getu Temesgen
በራሴ መቅጣት ልቻል
#ethiopia | በማስተዳድራቸው የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አካላትን በራሴ መቅጣት እንድችል የመንገድ ሀብት አጠቃቀም ደንብ አዘጋጅቻለሁ ሲል የአዲስ አበባከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ

በ2017 በጀት አመት 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቁሟል፡፡

ባለስልጣኑ እንዳስታወቀው በ2017 በጀት ዓመት ባለስልጣኑ በሚያስተዳድራቸው የመንገድ ሀብቶች ላይ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም በትራፊክ አደጋ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡

በበጀት ዓመቱ በመንገድ ሀብት ላይ 195 የትራፊክ አደጋ ሲደርስ ከደረሰው አደጋ 154 በቀለበት መንገዶች እንዲሁም 41 ከቀለበት መንገድ ውጪ ባሉ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

በ2017 ዓ.ም በደረሰው አደጋ 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ሊደርስ ችሏል፡፡

በመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርስ ጉዳት በህብረተሰቡ እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ ከመፍጠሩ ባሻገር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርሱ በባለስልጣን መስሪያቤቱ ባለስልጣኑ በሚያስተዳድራቸው የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አካላትን በራሱ መቅጣት የሚችልበትን የመንገድ ሀብት አጠቃቀም ደንብ ባለስልጣኑ አዘጋጅቶ በፍትህ ቢሮ ምልከታ እየተደረገበት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ደንቡ ሲፀድቅ መንገዶች ላይ ለሚደርሱ ጉዳቶች ባለስልጣኑ በራሱ ለመቅጣት ፍቃድ ስለሚያገኝ ለሚያከናውነው የመንገድ መሰረተ ልማቶች ደህንነትን የቁጥጥር ስራ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
#kgethiopia

12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.