ቢአኤካ ግሩፕ
#ethiopia | ቢአኤካ ግሩፕ ከቻይናው የካባድ መኪና ቀዳሚ አምራች ከሆነው ከግዙፉ ሻክማን ኩባንያ ጋር በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ (LNG) እንዲሁም በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ (EV) ከባድ መኪኖች ነገ ያስተዋውቃል።
ነገ ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ በተዘጋጀው የማስተዋወቂያ መድረክ የፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ (LNG) እንዲሁም በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የከባድ መኪኖችን (EV) ለኢትዮጵያ ገበያ ይፋ ይሆናሉ።
በቅርቡ በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ውስጥ የተበሰረውን የካሉብ የተፈጥሮ ጋዝ የመጀመሪያ ዙር ማምረቻን ተከትሎ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ መጭው ግዜ በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ መኪኖች ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡበት ሥርአት እንደሚዘረጋ የቀረጥ ነፃ ማበረታቻም እንደሚደረግ መግለፃቸው ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ ቻይና ሃገር የሚገኘው የሻክማን የመኪና አምራች ብቸኛ የኢትዮጵያ ወኪል የሆነውና ከዚህ ቀደም የሻክማንን የደረቅ፣ የፈሳሽ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ከባድ መኪኖችን ወደ ሃገራችንን በማስመጣት የሚታወቀው ቤአኤካ አዲስ ነገር ይዞ መጥቷል።
የሻክማንን መኪኖች በኢትዮጵያ ለመገጣጠም የሚያስችል የፋብሪካ ግንባታ በማጠናቀቅ ላይ የሚገኘው ቢአኤካ ግሩብ ከሻክማን ጋር በጋራ በመሆን ነገ ጥቅምት ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ የ X 3000, X 5000 እንዲሁም X 6000 ሞዴል በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ (LNG) እንዲሁም በኤሌክትሪክ(EV) ፍጆታ የሚሰሩና ግዜውን የዋጁ የከባድ መኪና ተሽከርካሪዎችን ያስተዋውቃል።
ይህንን የማስተዋወቅ ዝግጅት ለመታደም ከሰላሳ በላይ ከፍተኛ የቻይና መንግስት የሻንሽን ግዛት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የሻክማን ኩባንያ ከፍተኛ መሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል።
ይህ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በዛሬው እለት ቢአኤካ ዋና መስሪ ቤት በመገኘት ጉብኝት ያከናወነ ሲሆን በሁለቱ ግዙፍ ኩባንያዎች መካከል ከሚደረግ ትብብር ጎን ለጎን ከሻንሽን ግዛት መሪዎች ጋር ሰፋፊ የንግድና ኢንቨስትመንት አጋርነት ውይይቶች ተካሂደዋል።
ይህ ፕሮጀክት በኢትዮጵያን ከፍተኛ የሆነ የኢነርጅ ሽግግርን የሚያመጣ ቁልፍ ጅማሮ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ቢአኤካ በሚቀጥሉት ጥቂት ግዜያት ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራጭ ኃይል እንዲሁም በታዳሽ ኃይል የሚንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎችን ማየት እውን ይሆናል።

12 months ago