Logo
SeledaPost
የማር ጥቅሞች

1. ንጹህ ማር በቫይታሚን እና በተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ ሲሆን እነዚህ ቫይታሚኖች እና ንጥረ ነገሮችም ሰውነታችንን ከባክቴሪያዎች ይከላከላሉ፡፡

• ማር የሰውነታችንን የበሽታ መከላከል አቅም ይጨምራል፡፡
• ጉንፋን ሲይዘን እና የሚያስለን ከሆነ አንድ ወይም ሁለት የሻይ ማንኪያ ማር በትኩስ ውሃ ውስጥ መበጨመር አንዲሁም የተወሰነ ሎሚ እና ቀረፋ በማድረግ መጠቀም ይቻላል፡፡

2. ማርን በትኩስ ውሀ ውስጥ ከሎሚ ጋር በመጨመር ጠዋት ምግብ ከመውሰዳችን በፊት ከወሰድን በሰውነታችን ውስጥ የሚገኝ ቆሻሻን እና ቅባትን ያስወግዳል፤ የሰውነት ክብደትንም እንድንቀንስ ይረዳል፡፡

3. ማርን ከቀረፋ ጋር በመደባለቅ የምንወስድ ከሆነ የሰውነታችንን የኮሌስትሮል መጠን በ10 በመቶ መቀነስ እንችላለን

• አንድ የሻይ ማንኪያ ማር ከግማሽ የሻይ ማንኪያ ቀረፋ ጋር በትኩስ ውሃ ውስጥ ጨምሮ መጠጣት፡፡

4. በሀይል ሰጪነቱ ከፍተኛ ጥቅም ያለው ማር ከቡና ባልተናነሰ ሰውነታችን ያነቃቃል፡፡

5. ማር ለቆዳችን ልስላሴ እና ጥራት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

• በተጎዳው ቆዳ ላይ በመቀባት አንድ ሌሊት ማሳደር እና ጠዋት ጠዋት በንጹህ ውሃ መታጠብ ፡፡ ይህንን በተደጋጋሚ የምናደርግ ከሆነ ለስላሳ እና ንጹህ ቆዳ እንዲኖረን ይረዳናል፡፡

6. የምግብ አለመፈጨትን ይቀንሳል ፡፡

አንድ ወይም ሁለት የሾርባ ማንኪያ ማር ከበድ ያሉ ምግቦችን ከመመገባችን በፊት ብንወስድ አሊያም ምግብ ተመግበን የመክበድ ስሜት ከተሰማን በኋላ መውሰድ የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል፡፡via.zena.since

seledadotio
seledadotio
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.