Logo
SeledaPost
መረጃ ‼️

በአማራ ክልል ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመቋጨት ጥረት እያደረኩ ነው ሲሉ የክልሉ መንግሥት አስታወቀ፡፡

የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽ ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) ለጋዜጣ ፕላስ እንደተናገሩት፤ በክልሉ ያለውን ግጭት ለማስቆም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

በክልሉ ያለው ግጭት ሀብት፤ ንብረትና የሰው ነፍስ ላይ ውድመት እያደረሰ ነው፤ ግጭቱ እያደረሰ ያለውን ውድመት በማስቆም የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ግጭቱን በድርድር ለመፍታት እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል፡፡

ግጭቱን በድርድር ለማስቆም እየተሰራ ያለው ስራ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመቋጨት አመራሩን ከላይ እስከ ታች ድረስ የማደራጀት፤ የጸጥታ ኃይሉ ላይ ሪፎርም የመስራት፤ የሰላም ጥሪ የማድረግ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።(adnafta)

seledadotio
seledadotio
12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.