የኤች አይቪን ጨምሮ የጨጓራ መርመርያ ምርቶች የሚያመርተው ድረስም ድርጅት ስራ ጀመረ
#ethiopia | 500 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ቅጥራን ማኑፋክቸሪንግ ሜዲካል ኢኪዮፕመንት ትሬዲንግ ፒኤልሲ በይፋ ስራ ጀምሯል።
ድርጅቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በስሩ ከሚያስተዳድራቸው የኢንቨስትመንት ማዕከላት ውስጥ አንዱ ወደ ሆነው ቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በመግባት ለምርት ዝግጁ መሆኑን በዛሬው እለት ተገልጿል።
የቅጥራን ማኑፋክቸሪንግ ሜዲካል ኢኪዮፕመንት ትሬዲንግ ፒኤልሲ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አታኩሬ አያሌው እንደገለጹት ቅጥራን ማኑፋክቸሪንግ ሜዲካል ኢኪዮፕመንት ትሬዲንግ ፒኤልሲ የህክምና መሳሪያዎችን አምራች ሲሆን አሁን ባለው የሙከራ ስራ ኢደት 6 አይነት አጣዳፊ የህክምና መርጃ መሳሪያዎችን በማምረት ላይ ይገኛል ብለዋል።
አቶ አታኩሬ አክለውም ድርጅቱ የሀገር ውስጥ የህክምና መሳሪያዎች ምርትን በማብዛት የውጭ ምንዛሪን በማስቀረት ረገድ ሰፊ ድርሻን እንደሚይዝና አሁን ወደ ምርት ከገባ ጀምሮ የተለያዩ የጉበት የጨጓራ የኤች አይ ቪ መመርመሪያ ምርቶችን በማምረት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ቅጥራን ማኑፋክቸሪንግ ሜዲካል ኢኪዮፕመንት ትሬዲንግ ፒኤልሲ በቀን በሚሊየን የሚቆጠሩ የመመርመሪያ ኪቶችን የሚያመርትና አሁን ላይ በሙከራ ስራ ኢደት ለ50 ሰራተኞች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን በሙሉ አቅም ወደስራ ሲገባ 500 ሰራተኞችን የሚይዝ ይሆናል ተብሏል
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በመላው ሃገሪቱ ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው የኢንቨስትመንት ማዕከሎቹ ውስጥ ከ200 ባለይ የሃገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች የውጭ ምንዛሪ ግኝትን በማሳደግ፤ ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ፤ተኪ ምርቶችን በማምረት ፤ እንዲሁም በየአካባቢው ለሚገኙ አርብቶ እና አርሶ አደሮች ዘላቂ የሆነ የገበያ ትስስር በመፍጠር ላይ ይገኛሉ፡፡

8 months ago