እንኳን ለዓለም አቀፍ የቡና ቀን አደረሳችሁ!!!!
#ethiopia | ዛሬ በማለዳ ነቃሁ......ራሴን በመንፈሰ ከእናት ቡና ሥር ሰላም ለአንቺ አልኩኝ።
ቡና የኢትዮጵያ ምልክት በመሆኑም ደስ አለኝ!!!
ዛሬ ዓለም የቡና ቀን ተብሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል።
በግል በዓለም ዙሪያ እንዲህ ቀኑ ታሳቦ እንዲውል ነጥበ-መቅድም፣ የስሙ አሀዱ፣ የአጠራሩ አቡጊዳ፣ የሥርወ-ቃሉ መነሻ
ቡን-ቡና(Bun-Bunna) መንደር ፤ ኮፊ-ካፋ(Coffee-Kaffa) ዞን፤ ማኪራ በመንፈስ በማለዳ ተገኘሁ። እንዲህ ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሟ እንዲከበር ያለምንም መከልከል የፈጣሪን አሰራር አደነቅኩ። የእግዚአብሔርን ቸርነት በቡና እናት ላይ ስላደረገው መልካም ነገር ሁሉ ምስጋና አቀረብኩ።
አምላክ ሁኚ!!!! እንዳላት ቃሉን አክብራ እሷም እንዲሁ ሆነች።
ወደ ዓለም ሂጂ አህዛብን በሙሉ በመዓዛሽ ማወድ ይሁንልሽ፣ በጣዕምሽ የሰው ልጅን ታረኪው፣ መስተጋብሩ እንዲጠነክር፣ በአንቺ ምክንያት ፍቅር፣መጎዳኘት እንዲሆን....ቡና አቅምሺ ተብላ ስለተመረቀቺው እናት ቡና አሰብኩ። ዓለም በሙሉ ያከብርሻል፣ ስምሽንም ሱሰኛው በሙሉ ቡና ፣ኮፊ ብሎ ይጠራሻል ስለተባለቺው "ቡን እንዴ....ቡን ቱኬ ....እናት ቡና...ቡንቹም...ሱፐር ፕላንት (bunnchum-Super plant)" ሳስብ እውላለሁ።
ከቲፋ (የመጀመሪያው ገበያ) መነሻ መስክ በ-1990 ዓም ከሼክ ከድር(ነፍስ ይማር) ጋር ተቀመጠን ካሳዩኝ ሁለት የኦቶማን ቱርክ ጎራዴዎች ታሪክ ጋር የውይይቱን መንፈስ ከለስኩ። በሀሳቤ በማኪራ ከዋርካው ሥር የአባቶች ለአምላካቸው ስለ እናት ቡና ምርቃት ያቀረቡትን ትዝታውን መልሼ አዳመጥኩ።
ቡና ምግባችን ነው!!!( Coffee is our bread), ቡና ማንነታችን ነው!!!(Coffee is our identity) ብሎ ራሱን ስለሚጠራ የካፋ ሕዝብ አሰብኩ።
ቡና ከኢትዮጵያ መነሻ በመሆኑ እና ዛሬ ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ምርት ቀን የቡና ቀን ተብሎ በመከበሩ እንደ ኢትዮጵያዊ ኩራት ተሰማኝ።
በድጋሚ እንኳን ለዓለም አቀፍ የቡና ቀን አደረሰን!!!!
Solomon Tselele

9 months ago