አስመሳዩ 'ደህንነት' በቁጥጥር ስር ዋለ‼️
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት (NISS) አባል ነኝ እያለ ህብረተሰቡን ሲያስፈራራና ሲያግት ገንዘብ ሲቀበል የነበረ ግለሰብ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
ዳዊት ጥላሁን ወይም ምንተስኖት ጥላሁን የተባለው ተጠርጣሪ ሐሰተኛ የNISS መታወቂያ በመጠቀም ወንጀሉን ይፈጽም ነበር። ከህብረተሰቡ የመጣውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የአዲስ አበባ ፖሊስ በጋራ ባደረጉት ክትትል፣ ግለሰቡ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም በቁጥጥር ስር ውሏል።
ይህ ተጠርጣሪ ከሜክሲኮ ወደ ጋርመንት በታክሲ እየተጓዘች የነበረችውን ሳሮን ተስፋዬ የተባለች ግል ተበዳይን 'ደህንነት ነኝ' በማለት በማስፈራራት እና በመደብደብ ጉዳት ያደረሰባት ሲሆን፣ ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱ ይታወሳል። ፖሊስ ግለሰቡ በፈጸመው ጉዳት በህግ እንደሚጠየቅ አስታውቋል።
በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅትም ሐሰተኛ መታወቂያው ተይዟል።
ጥሪ ለህብረተሰቡ
የአዲስ አበባ ፖሊስ በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት የተፈጸመበት ግለሰብ ወይም ስለ ተጠርጣሪው ማንኛውም መረጃ ያለው ሰው ለመምሪያው በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
እንዲሁም፣ የጸጥታ አካላት አባል ነን በማለት የሚያስፈራሩና ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ግለሰቦች ሲያጋጥሙ በወቅቱ ለፖሊስ እንዲያሳውቁ መልዕክት አስተላልፏል።
የደህንነት አካል ነኝ ብለው የሚያስፈራሩ ግለሰቦችን ሲያጋጥም ምን ማድረግ እንዳለብዎ ያውቃሉ? ጥንቃቄ ያድርጉ እና ሪፖርት ያድርጉ!
Via AAP
seledadotio

9 months ago