ወደ አልጋነት የሚቀየር የፀሐይ ኃይል የተገጠመለት ቦርሳ!
የመኖሪያ ቤት እጦት ያለባቸውን ሰዎች ሕይወት ለመታደግ ያለመ አስገራሚ የፈጠራ ውጤት ከጀርመን ተመዝግቧል።
አንድ የጀርመን ስታርትአፕ (አዲስ ኩባንያ)፣ በአንድ ደቂቃ ውስጥ በቀላሉ ወደ ገለልተኛ አልጋነት የሚቀየር ቦርሳ (Backpack) ፈጥሮ ለገበያ ለማቅረብ እየተዘጋጀ ነው ተብሏል።
ይህ ሁለገብ ቦርሳ የጎዳና ላይ ኑሮን ፈታኝ ሁኔታዎች ለመቋቋም የሚያስችሉ ሁለት ወሳኝ ባህሪያትን አጣምሮ ይዟል።
ቦርሳው ሲገለበጥ ከቅዝቃዜ የሚከላከል እና በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ውስጥ ሙቀት የሚሰጥ ምቹ አልጋ ይሆናል ተብሏል።
ከቦርሳው ውጭ የተገጠሙት ፓነሎች በቀን ውስጥ ፀሐይን በመጠቀም ኃይል በመሙላት፣ የሞባይል ስልኮችን እና ሌሎች ጥቃቅን የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ለማብራት ይረዳሉ።
ኩባንያው ይህንን ፈጠራ "ተንቀሳቃሽ ቤት (A Mobile Home)" በማለት የሰየመው ሲሆን፣ በጎዳና ላይ ለሚኖሩ ሰዎች ከአደጋ የመከላከል እና የኑሮ ሁኔታን የማሻሻል ተስፋ ሰንቋል።
ይህ ፈጠራ ከዚህ ቀደም በሌሎች የአውሮፓ አገራት ከተሞከሩት Sheltersuit (ወደ መኝታ ቦርሳ የሚቀየር ኮት) እና በስኮትላንድ ተማሪ ተፈጥሮ በፀሐይ ኃይል የሚሞቅ ብርድ ልብስ ፅንሰ-ሀሳቦች ጋር የሚመሳሰል ሲሆን፣ ቴክኖሎጂን ከሰብዓዊነት ጋር ያጣመረ መፍትሄ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ዓይነቱ ፈጠራ በብዙ የጀርመን ከተሞች አጣዳፊ የሆነውን የጎዳና ላይ መጠለያ ችግር በከፊል ለመቅረፍ ይረዳል ተብሎ ይጠበቃል።
seledadotio

1 year ago