Logo
SeledaPost
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኑክሌያር ማብላያ ለመገንባት ተስማምተዋል።

የሩሲያው የዜና ወኪል TASS ን ጠቅሶ አናዶሉ ኤጄንሲ እንደዘገበው ሁለቱ ሀገራት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የኑክሌያር ጣቢያ ለመገንባት ተስማምተዋል።

ኑክሌየር የመገንባት ስምምነቱ በሩሲያ የኑክሌር ተቋም ሮሳቶም ዋና ሀላፊ አሌክሲ ሊኻቼቭ እና በኢትዮጵያው ውጭጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ መካከል ተፈርሟል።

በዚህም ኢትዮጵያን የኑክሌያር ጣቢያ ባለቤት የሚያደርጋትን ውል በፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፈቃድ መፈፀሙ ታውቋል።

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በ 2017 ኑክሌየርን ለሰላማዊ ጥቅም የመገንባት ስምምነትን መፈፀማቸው ለአሁኑ ስምምነት መሰረት መጣሉን አናዶሉ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በህዳሴው ግድብ ምረቃ ላይ ኢትዮጵያ የኑክሌያር ጣቢያ እንደምትገነባ መናገራቸው ይታወቃል።

seledadotio
seledadotio
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.