ኢራን በአስቸኳይ ዜጎችን መፍታት እንዳለብሽ አሳስባለሁ !/ኢማኑኤል ማክሮን/
የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለኢራን ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ መስጠታቸው ተሰማ ።
እሮብ እለት ከኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ጋር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ (UNGA) በኩል ውይይት ያደረጉት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ኢራን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሶስት የፈረንሳይ ዜጎችን በአስቸኳይ እንድትፈታ አሳስበዋል ቴህራን የኒውክሌር ግዴታዋን ማክበር እንዳለባት እና ቴህራን የኒውክሌር ማበልፀግ በአለምአቀፋዊው ህግ ተገዢ የመሆን ግዴታዋን ማክበር እንዳለባት አሳስበዋል።
ማክሮን በ X ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በለጠፈው ጽሁፍ ላይ "ከኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ጋር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ተገናኝቻለሁ።እንደተገናኘን በመጀመሪያ እና ከሁሉም በላይ ትኩረት ሰጠኋቸዉ ጥያቄዎች መካከልም በኢራን በእስር ላይ የሚገኙትን ሴሲል ኮህለር፣ ዣክ ፓሪስ እና ሌናርት ሞንቴርሎስ የተባሉትን ዜጎቻችን በዘፈቀደ የታሰሩና ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች እየተፈፀሙባቸዉ መሆኑን በመግለፅ በአስቸኳይ መፈታት እንዳለባቸው መግለፅ ነዉ" ሲል ጽፏል።
“ፈረንሳይ ልጆቿን በፍጹም አትተወም፤ አቋማችን ግልጽ ነው፤ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ማግኘት የለባትም” ሲሉ የፈረንሳይን ጽኑ አቋም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ማክሮን ከጀርመን እና ከእንግሊዝ ጋር የተቀናጀ ዕርምጃ እንደሚወሰድ በማሳወቁ የኢራንን የኒውክሌር ተገዢ አለመሆንን ጉዳይ ገልፀው ኢራን የኒውክሌር ግዴታዎቿን ካላሟላች አዲስ ማዕቀብ እንደሚጣልባት ገልፀዋል ።
የድርድሩን አስፈላጊነትን በማጉላት የተያገሩት ማክሮን "እኛ የማንደራደርባቸውን ጥያቄዎች ለኢራን ፕሬዝዳንት በድጋሚ ግልፅ አድርጌአለሁ፡ በኢራን ውስጥ የIAEA ተቆጣጣሪዎች ፍተሻ እንዲያደርጉ፣ የበለፀጉ የቁሳቁስ ክምችቶችን በተመለከተ ግልፅነት የተሞላበት መረጃ እንዲሰጡ እና ድርድር እንዲጀምሩ ነግሬያቸዋለሁ " ብለዋል።
"ለአካባቢው ደህንነት, ለአለም መረጋጋት ሲባል ጥቂት ሰዓታት ብቻ በቀሩት አድል እንድትጠቀም እመክራለሁ ቀሪዉ ላስቀመጥናቸው ህጋዊ ሁኔታዎች ምላሽ መስጠት የኢራን ጉዳይ ነው ። ሲሉ ተናግረዋል በማለት የዘገቡት ሮይተርስ ኢንዲያ ቢታይም ናቸዉ ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

9 months ago