አያ ጥራኝማ እና የሁለቱ ድምፃዊያን ዉዝግብ !
በተለቀቀ በአጭር ጊዜ በበርካቶች የተወደደዉና የተደመጠው "አያ ጥራኝማ" የተሰኘው ሙዚቃ የባለቤትነት ጉዳይ ዛሬም አወዛጋቢ ሁኖ ቀጥሏል ።
ድምፃዊት ሳምራዊት ባሳለፍነው እሁድ ወደሚዲያ በመቅረብ ሙዚቃው ከልጅነቷ ጀምሮ ስታዜመዉ እንደኖረች ግጥምና ዜማውም ከእሷ በፊት አለመሰራቱን መግለጿን ተከትሎ የሙዚቃው የባለቤትነት ጥያቄ ያቀረበችው የዘጠናዎቹ ተወዳጅ ድምፃዊት ቤተልሔም ዳኛቸው የሰነድና የሰዎችን ምስክርነት እማኝ በማድረግ ምላሽ ሰጥታለች ።
ድምፃዊቷ ወጣቷ ሳምራዊት ታዳጊ በመሆኗና
ለሁለቱም ቅርበት ያላቸዉ ወዳጆች ስለ ልጅቷ ህይወት ታሪክና የመጣችበትን ቅየ ጨምረው ለመስራት ያላትን ጉጉትና ምናልባት ስህተቱ የእሷ ላይሆን እንደሚችል በነገሯት መሰረት ከአመታት በፊት አልበሟ ላይ ተካቶ የነበረዉን አያ ጥራኝማ ዜማ ተፈጥሮ የነበረውን የኮፒራይት ጉዳይ በዝምታ ለማለፍ ሞክራ እንደነበር የገለፀችው ቤተልሔም ዳኛቸው ነገር ግን ሳምራዊት ከሰሞኑን በሚዲያ ላይ ቀርባ ምንም የተፈጠረ ነገር እንደሌለ አድርጋ መግለጿን ተከትሎ ጉዳዩን በህግ አግባብ እስከመጠየቅ እንደምትገፋበት ገልፃለች ።
በቃለ ምልልሱ ላይ የግጥምና የዜማ ደራሲዎች ምንም አይነት ክፍያ እንዳልከፈለቻቸዉ በመናገራቸው ማዘኗን የገለፀችው ቤተልሔም ደራሲዎች አብረዋት ያደጉና ከክፍያ ባሻገር ኪቦርድ በመግዛት ህይወታቸውን እንዲቀይሩ ማድረጓን ተናግራለች ።
በማህበራዊ ሚዲያ ባጋራችዉ መልዕክት" ደሞ በአይኔ መጣህን ከሰራሁ በሃላ ኢትዮጵያ ተመልሸ ስመጣ በእናት በአባቴ ቤት ሶስት ሁነው እየመጡ ብዙ ዜማዎችን ገዝቻቸው በተጨማሪ ኪቦርድ ገዝተው ሂወታቸውን እንዲቀይሩ የረዳሗቸው ሰዎች ናቸው።
የሰው ልጅ የበላበትን ወንጭት ሰባሪ ሁኖ በዚ ልክ ጭራሽ እኔኑ ገንዘብ ሳትከፍለን ማለታቸውን ስሰማ በቁማቸው መሞታቸውን ስለተረዳሁ ለእነሱ ከማዘን ውጭ በፍፁም አልተበሳጨሁም።" ስትል ፅፋለች ።
አክላም" ለማንኛውም በብዙ መረጃና በብዙ ምስክር ያስሉትን ስራ በቅንነት ለመተው ባስብ እንኳን ሌቦች የበላይ ሁነው ስላስቸገሩኝ በህግ ስም በማጥፋት ሳይቀር እጠይቃለሁ" ብላለች ።
እኛም በሁለቱ ወገን ለማጣራት ባደረግነው ሙከራ ድምዊት ቤተልሔም ዳኛቸው ይህንኑ ሙዚቃ ግጥም ለመዝፈን ከደራሲው ጋርና ከአንድ አሳታሚ ተቋም ጋር የተደረገ ዉልና ስምምነት እጇ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ችለናል ።

9 months ago