16 days ago
የሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 564 ተማሪዎች ተመረቁ
#ethiopia | ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 564 ተማሪዎችን በ17 የሙያ ዘርፎች ዛሬ በአዲስ ሲኒማ አዳራሽ አስመረቀ። ተቋሙ በሥራ ገበያው ፍላጎት ላይ ያተኮረ ተግባራዊ ስልጠና በመስጠት ተማሪዎችን ለሥራና ለራሳቸው የሥራ ዕድል ፈጠራ ማዘጋጀቱን ገልጿል።
ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ታዲዎስ ምስጋና በምረቃው መርሐ ግብር ላይ እንደገለጹት፣ ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከተቋቋመ አራት ዓመት ተኩል ያህል ቢሆነውም በዘርፉ ከረጅም ዓመታት የቆዩ ተቋማት ጋር በጥራት ተወዳድሮ እየሰራ ይገኛል። በዚህ ዓመትም በአዲስ አበባ ትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን በተካሄደው የስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ምዘና ከስልጠና ተቋማት መካከል አንደኛ መውጣቱን ገልጸዋል።
የዘንድሮው ምረቃ የተቋሙ አምስተኛ የምረቃ መርሐ ግብር ሲሆን፣ ተቋሙ በአምስት ዲፓርትመንቶች ወደ 17 የሚጠጉ የስልጠና ዘርፎችን እየሰጠ መሆኑን አቶ ታዲዎስ ገልጸዋል። ሴጅ ከገበያው ፍላጎት ጋር በማጣጣም አዳዲስ የስልጠና ዘርፎችን እያካተተ ሲሆን፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ጨምሮ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚፈለጉ ሙያዎችን በማስፋፋት ላይ ነው።
እንደ አቶ ታዲዎስ ገለጻ፣ ተቋሙ የስልጠና ዘርፎችን ሲመርጥ የገበያ ፍላጎትንና የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅምን መሠረት ያደርጋል። ተማሪዎች ስልጠናቸውን ከጨረሱ በኋላ ብቻ ተቀጣሪ ለመሆን ከመጠበቅ ይልቅ የራሳቸውን ሥራ መፍጠር እንዲችሉ ትኩረት እንደሚሰጥም ገልጸዋል።
በተለይም የጋዜጠኝነት ስልጠናው በሞባይል ጆርናሊዝም እና በዲጂታል መድረኮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቁመው፣ ተማሪዎች በዩቲዩብና ቲክቶክ ያሉ መድረኮችን ተጠቅመው የራሳቸውን ይዘትና ሥራ እንዲያዘጋጁ የሚያስችል ስልጠና እንደሚሰጥ አስረድተዋል።
ተቋሙ በተግባር የተደገፈ ስልጠናን ለማጠናከር የተማሪዎች የምረቃ ፕሮጀክቶች በዘርፉ ባለሙያዎች እንዲገመገሙ የሚያደርግ ሂደት መከተሉንም አቶ ታዲዎስ ጠቅሰዋል። ይህም ተማሪዎች ከቲዎሪ ባለፈ በተግባር የሚፈለገውን ክህሎት እንዲያዳብሩ ያግዛል ብለዋል።
ሴጅ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ሁለትና በአዳማ አንድ በድምሩ ሶስት ቅርንጫፎች እንዳሉት የገለጹት አቶ ታዲዎስ፣ በቀጣይ ቅርንጫፎችን በብዛት ከመክፈት ይልቅ የስልጠና ጥራትን ማስቀደም የተቋሙ ስትራቴጂ መሆኑን አመልክተዋል። ሴጅ በ10ኛ ዓመቱ በመላ ኢትዮጵያ ሰባት ቅርንጫፎች እንዲኖሩት ዕቅድ መያዙንም ገልጸዋል።
በምረቃው መርሐ ግብር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በመገንዘብ ለአቶ ብርሃኑ ዘርጋው የእውቅናና የምስጋና ሽልማት ተሰጥቷል። አቶ ብርሃኑ ዘርጋው የዘርጋው ክላውድ መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሲሆኑ፣ በክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ በኔትወርክና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ የተለያዩ ስራዎችን ሰርተዋል። በ2019 ዓ.ም. የተቋቋመው ዘርጋው ክላውድ ተመጣጣኝና አስተማማኝ የክላውድ መሠረተ ልማት ለማቅረብ እየሰራ ይገኛል።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
#sagetraininginstitute #graduation #ethiopia #education #vocationaltraining #skillsdevelopment #careerdevelopment #addisababa #students

Comments