15 days ago
የኔቶ አባል ሆና የጦር ሰራዊት የሌላት ብቸኛዋ ሀገር አይስላንድ
*በዚህች ሀገር ለሰዎች ትልቁ ስጋት ወንጀል ሳይሆን የተፈጥሮ አደጋ ነው
*በከተማው ያሉት ፖሊሶች መሳርያ አይዙም
#ethiopia | አይስላንድ የፖሊስ መኮንኖቿ መደበኛ የጦር መሣሪያ አይታጠቁም ይህም በዓለም ላይ ካሉ በጣም ሰላማዊ ሀገራት አንዷ ያደርጋታል።
አይስላንድ በዓለም ላይ ካሉ እጅግ ሰላማዊ ሀገራት አንዷ በመሆኗ በተደጋጋሚ በ"Global Peace Index" አናት ላይ ትገኛለች።
አይስላንድ ከ1869 ጀምሮ መደበኛ የጦር ሠራዊት የላትም።
የኔቶ (NATO) አባል ሀገር ብትሆንም መከላከያዋን በሌሎች አባል ሀገራት ድጋፍ እና በራሷ የባህር ጠረፍ ጥበቃ ነው የምታከናውነው።
የፖሊስ መኮንኖቿ በመደበኛነት የጦር መሣሪያ አይታጠቁም።
የጦር መሣሪያ የሚያስፈልግበት ሁኔታ ሲፈጠር እንኳን ፈቃድ ተጠይቆ ከልዩ የፖሊስ ክፍል ብቻ ነው የሚያገኙት።
ይህ አሠራር በህዝብ እና በፖሊስ መካከል ትልቅ መተማመን እንዲፈጠር አድርጓል።
በአይስላንድ ውስጥ ለሰዎች ትልቁ ስጋት ከሰዎች የሚመጣ ወንጀል ሳይሆን እንደ እሳተ ገሞራ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ወይም አስቸጋሪ የአየር ንብረት ያሉ የተፈጥሮ አደጋዎች ናቸው።
አይስላንድ በቱሪስቶች ዘንድ እጅግ ተመራጭ ከሚያደርጓት ነገሮች አንዱ ምንም ሳይሰጉ በማንኛውም ሰዓት በከተማዋ ወይም በተፈጥሮ ስፍራዎች መንቀሳቀስ መቻላቸው ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #icelandnato #worldpeaceindexes #themostpeacefulcountry

Comments