4 months ago
🎭 የሩሲያ የትያትር ጥበባት የልህቀት ሳምንት በአዲስ አበባ በይፋ ተጀመረ! 🇪🇹🇷🇺
በዓለም አቀፍ ደረጃ በትያትር ጥበብ ቀዳሚ ስም ያለው የሩሲያ የትያትር ጥበባት ኢንስቲትዩት (GITIS)፣ በአዲስ አበባ የልህቀት ሳምንት እና የልምድ ልውውጥ መርኃ-ግብር መጀመሩ ተበሰረ።
በዝግጅቱ ላይ ታዋቂ ምሁራን፣ ጸሐፍያነ ተውኔት እና የፊልም ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
የመርኃ-ግብሩ ዋና ዋና ነጥቦች፦
🤝 ትብብር፦
በአዲስ አበባ የሩሲያ የሳይንስ እና የባሕል ማዕከል ኃላፊ ቭላዲሚር ጎሎቫቼቭ እንደገለጹት፤ ዝግጅቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የባሕል እና የኪነ-ጥበብ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል።
🎓 ስልጠና፦
ለአንድ ሳምንት በሚቆየው ስልጠና የሩሲያ የትያትር ጥበባት ኢንስቲትዩት መምህራን እና ተመራማሪዎች መሰረታዊ እና ዘመናዊ የትያትር ክህሎቶችን ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና መምህራን ያካፍላሉ።
📍 ቦታ፦
ስልጠናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባሕል ማዕከል የሚካሄድ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች አዳዲስ የመድረክ ትወናና ዝግጅት፤ የትያትር ጥበብ ስልቶችን (Techniques) የሚቀስሙበት ይሆናል።
የሩሲያ የትያትር ጥበብ በተለይም እንደ ስታኒስላቭስኪ ያሉ ታላላቅ የሙያው ጠበብት ለዓለም የትወና ጥበብ መሰረት መሆናቸው ይታወቃል።
ይህ ስልጠና ለኢትዮጵያ የትያትር ዘርፍ አዲስ ትንፋሽ እንደሚሆን ይታመናል!
#theatretexcellence #ethiopiarussia #culturalexchange #addisababauniversity #gitis #artandculture #theatretraining #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን