6 months ago
ለትንሳኤ በዓል አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመጪው የትንሳኤ በዓል ደንበኞች የተረጋጋና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲያገኙ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማከናወኑን አስታውቋል። ተቋሙ በበዓሉ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የኃይል መቆራረጥና መዋዥቆችን ለመቀነስ በቴክኒክና በአደረጃጀት ረገድ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-
ተቋሙ በበዓሉ ዋዜማና ዕለት የኃይል መቆራረጥ እንዳይከሰት ለማድረግ የሚከተሉትን ተግባራት አከናውኛለሁ ብሏል፦
የመካከለኛና የዝቅተኛ ማሰራጫ መስመሮችን የመፈተሽና የረገቡ የኤሌክትሪክ ገመዶችን የመወጠር ስራ።
*የእንጨት ምሰሶዎችን በኮንክሪት የመቀየር ተግባር።
*የኃይል ጫና ያለባቸውን ትራንስፎርመሮች አቅም የማሳደግና አዳዲስ አጋዥ ትራንስፎርመሮችን የመትከል ስራ።
ብልሽቶች በሚከሰቱበት ወቅት አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በሁሉም የተቋሙ አደረጃጀቶች የአስቸኳይ ጥገና ግብረ-ኃይል ተዋቅሮ ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል። ይህም በበዓሉ ዕለት የሚፈጠሩ ችግሮችን በፍጥነት በመለየት መፍትሄ ለመስጠት ያስችላል ተብሏል።
በበዓሉ ዕለት በተመረጡ ማዕከላት የካርድ መሙላት አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለጸው ተቋሙ፣ ደንበኞች ግን የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች እንዲያደርጉ መክሯል፦
* ደንበኞች ያላቸው የኃይል መጠን (ዩኒት) ማለቅና አለማለቁን አስቀድመው እንዲያረጋግጡ።
* በበዓሉ ዕለት መጨናነቅ እንዳይፈጠር ቅድመ ክፍያ ካርዶችን አስቀድመው እንዲሞሉ ጥሪ ቀርቧል።
ደንበኞች ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዘ ማንኛውም ቅሬታም ሆነ መረጃ ሲኖራቸው በሚከተሉት አድራሻዎች መጠቀም ይችላሉ፦
* በስልክ መስመር፡ 905 ወይም 904
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ethiopia #easter #tensae #eeu #electricservice #news #addisababa

Comments