3 months ago
በማያውቁት የውጭ ሀገር ስልክ ቁጥር አይታለሉ!
⚠️ የጥንቃቄ መልዕክት
#ethiopia | በቴክኖሎጂ የታገዘ አዲስ የውጭ ሀገር ስልክ ማጭበርበር ስልት በመስፋፋቱ፣ ተጠቃሚዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተሳስቧል። "ዋንጊሪ" (Wangiri) ተብሎ የሚጠራው ይህ የማጭበርበሪያ ዘዴ፣ በአሁኑ ወቅት የብዙዎችን የስልክ ካርድና የባንክ ሂሳብ ለከፍተኛ ብክነት እየዳረገ ይገኛል።
ማጭበርበሩ እንዴት ይፈጸማል?
አጭበርባሪዎቹ ዘመናዊ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን በመጠቀም በሺዎች የሚቆጠሩ ስልኮችን በአንድ ጊዜ ይደውላሉ። ጥሪው አንድ ጊዜ ብቻ ጠርቶ ስለሚቋረጥ፣ ብዙዎች "ማን ይሆን የደወለው?" በሚል ጉጉት ተገፋፍተው መልሰው ይደውላሉ።
ሆኖም መልሰው ሲደውሉ በቀጥታ የሚገናኙት ከፍተኛ የክፍያ ተመን ካላቸው የውጭ ሀገር ቁጥሮች ጋር ነው። በጥሪው ላይ ረዘም ላለ ጊዜ እንዲቆዩ ለማድረግም፦
* ልዩ ልዩ ሙዚቃዎች ይከፈታሉ።
* የተቀዱ ድምጾች እንዲሰሙ ይደረጋል።
* በዚህ ሂደት ውስጥ በሴኮንዶች ውስጥ በስልካችሁ ላይ ያለው ካርድ ይሟጠጣል፤ የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ከሆናችሁ ደግሞ ከፍተኛ ዕዳ ውስጥ ይከታችኋል።
ሊታወቁ የሚገቡ የመለያ ኮዶች
የደኅንነት ባለሞያዎች በተለይ ከሚከተሉት የሀገር መለያ ኮዶች ለሚመጡ አጠራጣሪ ጥሪዎች ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል፦
+601፣ +993፣ +371፣ +370፣ +255፣ +375፣ +381 እና መሰል ኮዶች።
ራስዎን እንዴት ይከላከላሉ?
ከማጭበርበሩ ለመዳን ባለሞያዎች የሚከተሉትን የመከላከያ መንገዶች ይጠቁማሉ፦
* መልሰው አይደውሉ፦ የማያውቁትና የማይጠብቁት የውጭ ሀገር ጥሪ በአንድ ጥሪ ብቻ ከተቋረጠ በፍጹም መልሰው አይደውሉ ወይም ሜሴጅ አይላኩ።
* ቁጥሩን "Block" ያድርጉ፦ ተደጋጋሚ ጥሪዎችን የሚያደርጉ አጠራጣሪ ቁጥሮችን ወዲያውኑ በስልክዎ ላይ ይዘጉ (Block)።
* መረጃ ያጋሩ፦ ቤተሰብዎን እና ጓደኞችዎን ስለ ሁኔታው በማስረዳት ከጥቃት ይጠብቋቸው።
መልሰው መደወልዎ ካርድዎን ከማስበላቱም በላይ፣ ስልክዎ ንቁ እንደሆነ ለአጭበርባሪዎቹ ምልክት ስለሚሰጥ ለወደፊት ጥቃቶች ተጋላጭ ሊያደርግዎት እንደሚችል አይዘንጉ።
ባላወቁት ቁጥር መልሰው በመደወል የኪስዎን ገንዘብ ለአጭበርባሪዎች አያጋሩ!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #cybersecurity #wangiriscam #የስልክማጭበርበር #securityalert #ethiopia #techsafety