25 days ago
"ላሜን በዓይኔ እስካያት ድረስ ሰማዩንም ቢሆን አካልላለሁ!"
#ethiopia | በህንድ የሚገኝ አንድ አርሶ አደር የጠፋችውን ላሙን ለመፈለግ ዘመናዊ ካሜራ የተገጠመላት ድሮን መከራየቱ ተሰምቷል።
አርሶ አደሩ የጠፋችበትን ተወዳጅ ላሙን ለማግኘት ሲል ተስፋ ሳይቆርጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ለመጠቀም የወሰነ ሲሆን ከፍ ብላ የምትበርና ካሜራ የተገጠመላት ድሮን መከራየቱ ነው የተገለፀው።
ላሟ ለቤተሰቡ ተራ እንስሳ ብቻ አልነበረችም።
"በቤተሰባችን እጅጉን የምትወደድና የኢኮኖሚያችን መሠረት የሆነች የቅርብ ወዳጃችን ናት" ሲሉ አርሶ አደሩ በፍቅር ተናግረዋል።
እናም ይህችው ውድ ላም በአካባቢው ጥቅጥቅ ያለ ጫካና ሰፊ እርሻ ውስጥ ጠፍታ ስትቀር ባህላዊውን የእግር ጉዞ ፍለጋ ትተው ወደ አየር ላይ ፍለጋቸውን የቀጠሉት።
ድሮኗ ሰፊውን የገጠር መሬት ጫካዎችንና የወንዝ ዳርቻዎችን ከላይ ወደ ታች በከፍተኛ ጥራት ካሜራዋ መቃኘት ጀመረች።
ድሮኗ በሰማይ ላይ ስታንዣብብ የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች አዲስ የሳይንስ ፊልም እየተቀረፀ መስሏቸው በጉጉትና በደስታ ሰማይ ሰማዩን ይመለከቱ ነበር።
የድሮኗ ኦፕሬተር ከላይ የሚመጣውን ምስል እየተከታተለ አርሶ አደሩን "ይህችኛዋ ላም ያንተ ናት?" እያለ ያሳየው ነበር።
ምስጋና ለቴክኖሎጂ ይግባና ተወዳጇ የአርሶ አደሩ ላም ከብዙ አድካሚ ፍለጋ በኋላ ጥቅጥቅ ባለ ጫካ ውስጥ ልትገኝ ችላለች።
ይህ አጋጣሚ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለትልልቅ ከተሞችና ለትልቅ ምርምር ብቻ ሳይሆን ለገጠሬው ማህበረሰብም ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል ያሳየ ክስተት ሆኗል።
"ላሜን በዓይኔ እስካያት ድረስ ሰማዩንም ቢሆን አካልላለሁ" ያለው አርሶ አደሩም ቀመጨረሻ ድካሙ ፍሬ አፍርቶለታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #dronesearch #lostcow #indianews #techinfarming #dronetechnology

Comments