2 days ago
ዘምዘም ባንክ 5ኛ ዓመቱን በተለያዩ መርሐ ግብሮች አከበረ
#ethiopia | ዘምዘም ባንክ የተመሠረተበትን 5ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ “በማይነጥፍ ጽናት ወደ ላቀ ምዕራፍ” በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በተለያዩ መርሐግብሮች አክብሯል።
በዓሉን አስመልክቶ IFB Pioneers Forum እና “ዘምዘም ሪሚት” የተሰኘውን ዲጂታል የሐዋላ አፕሊኬሽን አስመርቋል።
በመርሐግብሩ የተመረቀው “ዘምዘም ሪሚት” አፕሊኬሽን በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፈጣንና ደህንነቱ የተጠበቀ የሐዋላ አገልግሎት የሚያቀርብ ሲሆን፣ ተጨማሪ የሐዋላ ክፍያ እንዳይከፈል እና ለተቀባዩ ተጨማሪ “ሂባ” እንዲሰጥ ያስችላል።
ባንኩ ከ“ዘምዘም ሪሚት” በተጨማሪ የዲጂታል ለውጡን ለማፋጠን የንብረት አስተዳደር፣ የአባልነት አስተዳደር፣ ዲጂታል የሂሳብ ክፍት ሥርዓት፣ Virtual Data Room፣ Internet Banking እና Salary Advance System የተሰኙ ስድስት የዲጂታል ሥርዓቶችን ሥራ ማስጀመሩን አስታውቋል።
ባንኩ በቀጣይ የዲጂታል ለውጡን በማፋጠንና ከሸሪዓ መርሆች ጋር የተጣጣሙ አዳዲስ የፋይናንስ መፍትሔዎችን በማስፋፋት በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ከወለድ ነፃ ባንክ ዘርፍ ያለውን አስተዋጽዖ ለማሳደግ እንደሚሰራ አስታውቋል።
#zamzambank #ethiopia #ifb #islamicbanking #zamzamremit #digitalbanking #remittance #financialinclusion #shariahcompliantbanking

Comments