3 months ago
የኢትዮጵያ የመድኃኒት ሉዓላዊነት፡ ከውጭ ጥገኝነት ራስን ወደ መቻል የሚደረግ ሽግግር
*******************
ኢትዮጵያ የመድኃኒት ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እያደረገችው ያለው ጉዞ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።
ሀገራችን መድኃኒትን ማምረት እንደ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ብቻ ሳይሆን እንደ ብሔራዊ የህልውና እና የሉዓላዊነት ጉዳይ በመቁጠር ስትራቴጂካዊ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች።
በተለይም በቅርቡ የተመረቀው የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) በላቁ ላቦራቶሪዎቹ እና በባዮኢኩቫለንስ ማዕከሉ ለዘርፉ የቴክኒክ ጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለግላል።
ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተገኘው ትምህርት የኢንዱስትሪ ፖሊሲያችንን የቀየረ ሲሆን፣ ከ90 በመቶ በላይ የነበረውን የውጭ ጥገኝነት በመቀነስ በአሁኑ ወቅት የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርት ብሔራዊ ፍላጎቱን 44 በመቶ መሸፈን ችሏል።
ይህ አቅም በቅርብ ጊዜ ውስጥ 55 በመቶ ለማድረስ በቁርጠኝነት እየተሠራ ይገኛል።
በተጨማሪም የ"ShieldVax Enterprise" ፕሮጀክት ኢትዮጵያን የክትባት ምርት ማዕከል ለማድረግና ከጥሬ ዕቃ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ የማምረት (End-to-End manufacturing) ግብ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ነው።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተመዘገበው የ58 በመቶ የተኪ ምርት አፈጻጸም ለጤናው ዘርፍ ትልቅ ተስፋን የሰጠ ነው።
በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ራስን ለመቻል የተቀመጠው ግብም በሳይንሳዊ ምርምርና በቴክኖሎጂ የታገዘ በመሆኑ ስኬቱ እውን መሆኑ አይቀሬ ነው።
የኢትዮጵያ ዕድገት በዜጎች ጤና እና በምርታማነት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ይህ የሉዓላዊነት ጉዞ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ስለ ትንታኔው ዝርዝር መረጃ አስተያየት መስጫው ውስጥ ካለው ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
🔗
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #pharmaceuticalsovereignty #healthcareindependence #ahri #shieldvax #selfsufficiency

Comments