7 months ago
ታዋቂው የሙዚቃ ጣቢያ MTV ስርጭት አቆመ
📌የዲጂታሉን ዓለም መገዳደር አልቻለም
#ethiopia | ለተከታታይ አራት አስርት ዓመታት የዓለምን የሙዚቃ ኢንዱስትሪና የፖፕ ባሕል (Pop Culture) ሲመራ የቆየው ታዋቂው MTV፣ የቴሌቪዥን ስርጭቱን ስለማቆሙ መረጃዎች እየወጡ ነው።
ጣቢያው በተለይም በፈረንጆቹ 1980ዎቹ እና 90ዎቹ የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ለዓለም በማስተዋወቅና የበርካታ ታዋቂ አርቲስቶችን ስም በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና ነበረው።
ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተመልካቾች ወደ ዲጂታል አማራጮች እንደ YouTube እና TikTok መዞራቸው ለጣቢያው መዳከም ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተመልክቷል።
የስርጭቱ መቋረጥ ምክንያቶች፡-
* የዲጂታል አማራጮች መስፋፋት፡ ተመልካቾች የሙዚቃ ቪዲዮዎችን በቴሌቪዥን ከመጠበቅ ይልቅ በማንኛውም ሰዓት በኢንተርኔት ማግኘታቸው።
* የተመልካች ቁጥር መቀነስ፡ የወጣቱ ትውልድ ትኩረት ከባህላዊ የኬብል ቴሌቪዥን ወደ ማህበራዊ ሚዲያዎችናየቀጥታ ስሬጭቶች አገልግሎቶች መሸጋገሩ።
* የይዘት ለውጥ፡ MTV ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሙዚቃ ይልቅ በሪያሊቲ ሾው (Reality Shows) ላይ ማተኮሩ የነበረውን ተቀባይነት እንዲቀንስ አድርጎታል።
MTV እ.ኤ.አ. ነሐሴ 1 ቀን 1981 ስርጭቱን ሲጀምር የመጀመሪያው የቪዲዮ ሙዚቃ "Video Killed the Radio Star" እንደነበር ይታወሳል። አሁን ላይ ደግሞ የኢንተርኔት ዓለም በቴሌቪዥን ስርጭቱ ላይ ተመሳሳይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።
ምንም እንኳን ቴሌቪዥን ስርጭቱ ቢቆምም፣ ብራንዱ በዲጂታል መድረኮች እና በተለያዩ ዝግጅቶች (እንደ MTV VMAs ሽልማት) ህልውናውን ሊቀጥል እንደሚችል ይገመታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#mtv #musictelevision #popculture #musichistory #mediashift #ripmtv #digitalera

Comments