Logo
Getu Temesgen
የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል ብር 5.6 ቢሊዮን ደረሰ
#ethiopia | አዲስ ባንክ አ.ማ. እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2025 ዓ.ም. በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በሁሉም ዋና ዋና የሥራ የአፈጻጸም መለኪያዎች ታሪካዊ እድገት ማስመዝገብ ቻለ።

የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል ብር 5.6 ቢሊዮን እንዲሁም የተከፈለ ካፒታል ብር 2.5 ቢሊዮን መድረስ ችሏል።

ከዚህም በላይ ባንኩ በተያዘው ሂሳብ ዓመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት ውስጥ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ አክስዮኖች መሸጥ የቻለ ሲሆን በዚህም የተከፈለ ካፒታሉን ወደ ብር 3.1 ቢሊዮን ማሳደግ ችሏል፡፡

ይህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የብር አምስት ቢሊዮን ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሟላት በትክክለኛው መንገድ ላይ እንደሚገኝ ማሳያ ነው፡፡

ባንኩ በጠንካራ የገቢ እድገትና ጥንቃቄ የተሞላበት የወጪ አጠቃቀም ከታክስ በፊት የተገኘውን ትርፍ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ397 በመቶ በማሳደግ ብር 2.9 ቢሊዮን እንዲሁም ከታክስ በኋላ የተገኘው የተጣራ ትርፍ ብር 2.2 ቢሊዮን ሆኗል።

በዚህም ባንኩ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ የአክስዮን ትርፋ ድርሻ ማለትም 92.43 በመቶ እንዲሁም 57.37 በመቶ የትርፍ ክፍፍል መስጠት ችሏል፡፡

በሌላ በኩል ባንኩ የእይታ ገጽታውን ለማዘመንና የደንበኞችን አገልግሎት ለማሻሻል የገጽታ ስም ለውጥ (rebranding) ያደረገበት ታሪካዊ ወቅት ነበር።

የዚህ ጥረት አካል የሆነው እና የባንኩን የወደፊት ማንነቱን የሚያንጸባርቁ አዲስ አርማ፣ የታደሰ መፈክር እና የሥም ማሻሻያዎችን አስተዋውቋል።

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.