6 months ago
🏟️ "በ2028 ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ወደ ኢትዮጵያ እናመጣለን!" - ፒርስ ኦክላጋን 🇪🇹🏃🏽♂️
#ethiopia | "አደይ አበባ ስታዲየም ከተጠናቀቀ የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ኮም ይመጣሉ"
የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በጋራ በሰጡት መግለጫ ታላቅ የምስራች አብስረዋል።
የዳይሬክተሩ ዋና ዋና ነጥቦች:
ዓለም አቀፍ ውድድር በኢትዮጵያ:
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለማዘጋጀት በቂ አቅም እንዳላት የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ "የ2028 የሶስት ቀን ውድድርን (Ultimate Championship) ጨምሮ ሌሎች ውድድሮችን ወደ ኢትዮጵያ እናመጣለን" ብለዋል።
የቤት ስራው:
ይህ እውን እንዲሆን ግን በመገባደድ ላይ የሚገኘው አደይ አበባ ዓለም አቀፍ ስቴዲየም እና ሌሎች የአዲስ አበባና አቃቂ ቃሊቲ ፕሮጀክቶች በፍጥነት ተጠናቀው ለውድድር ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስበዋል።
ትልቅ ጉብኝት:
የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሎርድ ሰባስቲያን ኮ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡም ተናግረዋል።
የፌዴሬሽኑ ዝግጁነት:
ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በበኩላቸው፤ የተጀመረው የስፖርት ዲፕሎማሲ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ተወካይ እንዲኖራት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
መንግስትም የስታዲየም ግንባታዎቹን እንዲያፋጥን ጥሪ አቅርበዋል።
በመጨረሻም ለዳይሬክተሩ የባህል ልብስ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
ጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ
#worldathletics #ethiopia #adeyabebastadium #sileshisihine #pierceocallaghan #sportsdiplomacy #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Comments