14 days ago
የሕንድ ማላንካራ ፓትርያርክ በቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
♦️ ቅዱስ ፓትርያርኩ በዘንድሮው የመስቀል ደመራ ይገኛሉ
#ethiopia | የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ በዛሬው እለት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ደማቅ መንፈሳዊ አቀባበል ተደረገላቸው።
የፓትርያርኩ ልዑካን ቡድን በካቴድራሉ ሲደርስ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን በዝማሬና በመንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተቀብለዋቸዋል።
የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት እንደዘገበው፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በእንኳን ደህና መጡ ንግግራቸው ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ጥንታዊ አኃት አብያተ ክርስቲያናት በመሆናቸው በየጊዜው መገናኘትና መወያየት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።
ፓትርያርኩ ከአሥር ዓመት በፊት እሳቸውና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሕንድ ያደረጉትን ጉብኝት በማስታወስ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ የኢትዮጵያን ጥሪ አክብረው በአገሪቱ መገኘታቸው ደስ እንደተሰኙ ገልጸዋ በቆይታቸውም ኢትዮጵያን በጸሎታቸው እንዲያስቡ ጠይቀዋል።
በምላሻቸው የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ በማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በካህናትና በምእመናን ስም ሰላምታቸውን አቅርበዋል። ከአሥር ዓመት በፊት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በሕንድ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት እሳቸው በቅርበት በማስተናገድና ጉብኝቱን በማስተባበር ተሳትፈው እንደነበር አስታውሰዋል።
የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት እንደዘገበው፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ይህ በካቴድራሉ የሚያደርጉት ሁለተኛ ጉብኝታቸው መሆኑን ጠቅሰው፣ ቀደም ሲል የቀድሞው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው እንደነበር ገልጸዋል።
ፓትርያርኩ በዓለም ዙሪያ ባደረጓቸው ሐዋርያዊ ጉዞዎች መካከል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያገኙትን አቀባበል በልዩ ሁኔታ አድንቀዋል። በካቴድራሉ የቀረበላቸው ዝማሬና ክብር ልባቸውን በጥልቅ እንደነካ ተናግረዋል።
በተጨማሪም በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ጥንታዊ ታሪካዊና መንፈሳዊ ትስስር በማስታወስ፣ ቀደምት የሕንድ መምህራን በኢትዮጵያ መንፈሳዊ ሴሚናሪዎች እንዳስተማሩ ጠቁመዋል። ወደፊትም በሴሚናሪዎች ደረጃ የተማሪዎችና የመምህራን ልውውጥ እንዲኖር፣ በነገረ መለኮት፣ በባህልና በሥርዓተ አምልኮ ዙሪያም በበለጠ በጋራ ለመሥራት ግንኙነቱን ማጠናከር እንደሚገባ አስረድተዋል።
በአቀባበሉ መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኃላፊዎች፣ ሊቃውንትና በርካታ ምእመናን ተገኝተዋል። መርሐ ግብሩም በብፁዓን ቅዱሳን አባቶች የጋራ ጸሎትና ቡራኬ ተጠናቋል።
የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት እንደዘገበው፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ ከመስከረም 14 እስከ 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በሚኖራቸው የአምስት ቀናት የኢትዮጵያ ቆይታ የተለያዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብሮችን ያከናውናሉ።
በመስከረም 15 ቀን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና አካላት ጋር የሁለትዮሽ ውይይት የሚያካሂዱ ሲሆን፣ በመቀጠልም እንጦጦ ቅድስት ማርያም ሙዚየምና ሰበታ ቤተ ደናግል ጠባባት ገዳምን ይጎበኛሉ።
በዘንድሮ የመስቀል ደመራ በዓል መስከረም 16 ቀን በመስቀል አደባባይ በመገኘት ቃለ ምዕዳንና ሐዋርያዊ ቡራኬ እንደሚሰጡም ተገልጿል። መስከረም 17 ቀን ጠዋት ደግሞ በቦሌ ደብረ ሣሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል በመገኘት ሥርዓተ ቅዳሴ እንደሚያደርጉ የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት ዘግቧል።
#ethiopia #orthodoxtewahedo #ethiopianorthodoxchurch #malankaraorthodox #baseliosmarthomamathewsiii #patriarch #abunemathias #holytrinitycathedral

Comments