30 days ago
🚗 ካቮድ 2 ዘመናዊ መኪኖችንና የቤት ዕቃዎችን ለዕድለኛ ደንበኞቹ ሸለመ
በካናዳ የሚኖሩ የዲያስፖራ ደንበኛም የአንዷ መኪና ባለዕድል ሆነዋል!
ካቮድ ኮሜርሻል ሪል እስቴት ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው “የካቮድ ልዩ ሎተሪ” እጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት፣ 2 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችንና የቤት ዕቃዎችን ለዕድለኛ ደንበኞቹ አበረከተ።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ባለሙያዎች በተገኙበት በተካሄደው እጣ አወጣጥ፣ ከ2ቱ መኪኖች አንዷን ያሸነፉት በካናዳ የሚኖሩ የዲያስፖራ ደንበኛ ሆነዋል።
🏠 በተጨማሪም እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኦቪድ ፈርኒቸር የቤት ዕቃዎች ለዕድለኛ ደንበኞች ተሸልመዋል።
ከ300 በላይ ደንበኞችና እንግዶች በታደሙበት በዚሁ መርሃ ግብር፣ “አራዳው ነጋዴ” የተሰኘው የካቮድ አዲስ ብራንድም በይፋ ተዋውቋል።
የካቮድ ኮሜርሻል ሪል እስቴት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የምወድህ ታደለ፣ የካቮድ የንግድ ስኬት መሠረቱ የደንበኞች እምነትና ድጋፍ መሆኑን ገልጸዋል።
“ካቮድ የንግድ ቦታ አቅራቢ የሪል እስቴት ኩባንያ ብቻ ሳይሆን፣ ደንበኞቹ ሀብትና የንግድ ስኬት እንዲገነቡ የሚያግዝ አጋር ነው” ብለዋል።
የኦቪድ ሆልዲንግስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ኦፊሰር አቶ መኮንን ተሾመ በበኩላቸው፣ የኩባንያዎቹ የንግድ ፍልስፍና በደንበኛ እምነት፣ በጥራትና በረጅም ጊዜ አጋርነት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ጠቁመዋል።
✨ “ዛሬ የተገናኘነው እጣ ለማውጣት ብቻ ሳይሆን፣ ከደንበኞቻችን ጋር የገነባነውን እምነት ለማክበር ነው” ብለዋል።
#kavod #kavodcommercialrealestate #ovidholdings #ካቮድ #ሎተሪ #አራዳውነጋዴ #realestate #ethiopia

Comments