4 months ago
የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ (Brent Crude) በአንድ በርሜል 115.7 ዶላር ገብቷል
#ethiopia | በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ወታደራዊ ፍጥጫ ወደ ለየለት ምድር ላይ ወረራ እያመራ ነው መባሉን ተከትሎ፣ የዓለም የነዳጅ ገበያ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወድቋል።
አሜሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ እግረኛ ወታደሮቿን ወደ ኢራን ለማስገባት የምድር ላይ ዘመቻ እቅድ እያዘጋጀች ነው የሚሉ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ። ይህንን ተከትሎ የኢራን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ መሀመድ ባገር
"ጠላት በግልጽ ስለ ድርድር እያወራ በጓሮ ወረራ እያቀደ ነው፤ እኛ ግን የአሜሪካ ወታደሮች መሬታችንን እስኪረግጡ በጉጉት እየጠበቅን ነው፤ መጥተው በእሳት እንዲነዱና እንዲቃጠሉ እናደርጋቸዋለን" ሲሉ ዝተዋል።
ይህ ወታደራዊ ውጥረት በነዳጅ ገበያው ላይ እሳት ጭሯል። በዚህም መሠረት፦
* የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ (Brent Crude): በአንድ በርሜል 115.7 ዶላር ገብቷል።
* የአሜሪካ ዌስት ቴክሳስ (WTI): ዋጋው ወደ 102 ዶላር ከፍ ብሏል።
የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚተነብዩት ከሆነ፣ ውጥረቱ ሳይረግብ እስከ ሰኔ ወር ድረስ የሚቀጥል ከሆነ የአንድ በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 200 ዶላር ሊደርስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ይህም በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የዋጋ ጭማሪ ሊሆን ይችላል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #የነዳጅዋጋ #ኢራንእናአሜሪካ #የዓለምኢኮኖሚ #ሰበርዜና #middleeasttension #oilpricehike

Comments