4 months ago
ኢራን ለትራምፕ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጠች
* "የጦር ኃይላችን ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነው"
#ethiopia | የኢራን ዋና ተደራዳሪ መሀመድ ባገር ጋሊባፍ ዩናይትድ ስቴትስ ኢራንን ከማስፈራራት እንድትቆጠብ እሁድ ዕለት ጠንካራ ማስጠንቀቂያ የሰጡ ሲሆን፣ "የጦር ኃይላችን ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነው" ሲሉ ዝተዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ለሒዝቦላህ የምታደርገውን ድጋፍ አስመልክቶ ጥቃት ለመሰንዘር ከዛቱ በኋላ ጋሊባፍ ሲናገሩ፤ “ዛቻቸው ፍሬ የሚያፈራ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ካሉበት የሽንፈት ደረጃ ላይ እንደማይደርሱ አያስቡም? እኛ የአሜሪካን ዛቻ ከግምት ውስጥ አናስገባም” ብለዋል።
ትራምፕ ቀደም ሲል በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፥ ኢራን ከፍተኛ ክፍያ የምትከፍላቸው በሊባኖስ የሚገኙ ተላላኪዎቿ ሁከት መፍጠራቸውን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ካላደረገች፣ ልክ ባለፈው ሳምንት እንደተደረገውና ከዚያም በበለጠ ሁኔታ ኢራንን በኃይል እንመታታለን ሲሉ አስፈራርተው ነበር።
የጋሊባፍ አስተያየት የተሰማው አሜሪካና ኢራን በስዊዘርላንድ በፓኪስታን እና ኳታር አደራዳሪነት ውይይት እያደረጉ ባሉበት ወቅት ሲሆን፣ ሀገራቱ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ አንቀጽ 1 ላይ አንዳቸው በሌላው ላይ ኃይል ከመጠቀም ወይም ከመዛት ለመቆጠብ ቃል ገብተው ነበር።
ይሁን እንጂ የኢራኑ ፋርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው የትራምፕ ዛቻን ተከትሎ የሰላም ንግግሩ እንዲቋረጥ ምክንያት ሆኗል ቢልም፣ ይህ መረጃ እስካሁን በማንኛውም ይፋዊ አካል አልተረጋገጠም።
#iranvsusa #donaldtrump #ghalibaf #middleeasttension #breakingnews #peacetalks #hezbollah

6 months ago
የዓለም ነዳጅ ዋጋ ናረ
* የጦርነት ደመና በመካከለኛው ምስራቅ እያንዣበበ ነው!
#ethiopia | ዓለም አቀፉ የፖለቲካ ውጥረት የኢኮኖሚ ቀውስ እየወለደ ነው! በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ፍጥጫ ዛሬ አርብ የነዳጅ ዋጋን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር አድርጎታል።
ብሬንት ነዳጅ (Brent Crude)፦
በ1.17% በመጨመር አንድ በርሜል $106.3 ደርሷል።
WTI ነዳጅ፦
በ1.12% አድጎ $96.92 ሆኗል።
የኢራን ኮማንዶዎች በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የንግድ መርከብ መቆጣጠራቸውና በቴህራን ሰማይ ላይ የአየር መከላከያ ሚሳይሎች ተኩስ መጀመሩ ስጋቱን ከፍ አድርጎታል።
በአሜሪካና በኢራን መካከል ያለው ድርድር መቋረጡን ተከትሎ፣ ተንታኞች አሁን ያለው ሁኔታ "ወደ ጦርነት ለመግባት የሚደረግ የዝግጅት ምዕራፍ" እንደሆነ እያስጠነቀቁ ነው። ግጭቱ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ የነዳጅ ዋጋ የዓመቱን ከፍተኛ ጣራ (Record) ሊሰብር እንደሚችል ተገምቷል።
ይህ የነዳጅ ዋጋ ንረት በቀጥታ ወደ ኪሳችን ነው የሚመጣው። የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት ማለት የዓለም ኢኮኖሚ መታፈን ማለት ነው። ትራምፕና የኢራን መሪዎች ለዚህ ፍጥጫ ምን ዓይነት መፍትሄ ይሰጡ ይሆን? ወይስ ዓለም ሌላ ጦርነት ልታስተናግድ ነው?
የነዳጅ ዋጋው ከጦርነቱ ድምጽ በላይ እየጮኸ ነው!
#getu #oilpricespike #middleeastconflict #iranvsusa #hormuzstrait #globaleconomy #breakingnews #energycrisis #ነዳጅ #የነዳጅዋጋ #ኢራን #ጦርነት #ኢኮኖሚ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments