1 month ago
የሰጪነት ልግስና እና የባሕር በር እቅብነት፤ የምስራቅ አፍሪካ የታሪክ እና የፍትሕ ተቃርኖ
*************************
ኢትዮጵያ በርካታ ድንበር ተሸጋሪ ወንዞች ባለቤት በመሆኗ ከከፍታማው የመካከለኛው ደጋ ክፍሏ የሚፈልቁት እነዚህ ተፈጥሯዊ ሀብቶች ወደ ተለያዩ የጎረቤት ሀገራት በመፍሰስ ለቀጣናው ህዝቦች የመጠጥ፣ የእርሻ እና የኃይል ምንጭ ሆነው በማገልገል ትልቅ በረከት ሆነዋል።
አገራችን ችግኝ በመትከል፣ የአፈርና ውሃ ጥበቃ በማድረግ እንዲሁም የተፈጥሮ ሀብትን በመንከባከብ ለወንዞቹ የምትንከባከብ ሲሆን የዓባይ፣ የተከዜ፣ የባሮ አኮቦ፣ የዋቢ ሸበሌ፣ የገናሌ ዳዋ እና የኦሞ ወንዞች ለግብጽ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኬንያ እና ደቡብ ሱዳን ህይወትና የልማት መደገፊያ ሆነዋል።
የወንዝ ውሃ ቀጥታ ለማያገኙት እንደ ጅቡቲ ላሉ ጎረቤቶች ደግሞ በቧንቧ ፕሮጀክቶች የመጠጥ ውሃና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ተፈጥሯዊ ሀብቷን በፍትሃዊነትና በወንድማማችነት እያካፈለች ትገኛለች።
ሆኖም ግን በዚህ በጎነት እና ሰጪነት ውስጥ ትልቅና አስገራሚ የታሪክ ተቃርኖ ይታያል። ኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ ሀብቷን ለጎረቤቶቿ ህይወትና ልማት ያለ ምንም ስስት በልግስና እያካፈለች፣ ለቀጣናው የጋራ እድገትና ትስስር አወንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከተች፣ ወደ ቀይ ባሕር ታሪካዊና ህጋዊ መብቷ ለመመለስና የባሕር በር ፍላጎቷን በፍትሃዊነት ለማረጋገጥ ስትጠይቅ በጎ ምላሽ አለማግኘቷ አሳዛኝ ተቃርኖ ነው።
የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ከኢትዮጵያ የሚወጡትን ወንዞች በመጠቀም መጠነ-ሰፊ የልማት ስራዎችን ሲከውኑና የኤሌክትሪክ ኃይል ሲያገኙ፣ የኢትዮጵያን ህጋዊ የባሕር በር ጥያቄ ለማደናቀፍ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መኖራቸው በቀጣናው የጋራ ልማት እና ፍትሕ ላይ ጥላ ያጠላ አግባብ ያልሆነ አካሄድ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዳነሱት፣ ከኢትዮጵያ የሚመነጩትና ድንበር ተሸግረው የሚወጡት ወንዞች ለጎረቤት ሀገራት ህዝቦች ልማትና እድገት በረከት እንደመሆናቸው መጠን፣ ኢትዮጵያም ከቀይ ባሕር ማግኘት የሚገባትን ህጋዊና ታሪካዊ መብት ማግኘት ይገባታል።
ወደፊትም በቀጣናው ዘላቂ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማረጋገጥ፣ ኢትዮጵያ የምትታወቅበትን ሰጪነትና የፍትሃዊነት መርህ ጎረቤቶችም በሰጥቶ መቀበል መርህ ምላሽ ሊሰጡበትና የባሕር በር ፍላጎቷን በጋራ ተጠቃሚነት መፍታት ይኖርባቸዋል።
በመሀመድ ፊጣሞ
#ethiopiaredseaaccess #transboundarywaters #hornofafricadiplomacy #fairequitableuse #regionalintegration

Comments