1 month ago
የኢትዮጵያን የሕክምና ዘርፍ የሚያዘምን የዲጂታል ኢንቨስትመንት መርሐ ግብር ይፋ ሆነ
********************
የጤና ሚኒስቴር ሀገራዊ የሕክምና ዘርፍ በቴክኖሎጂ ለማዘመንና የኢንጂነሪንግ ሕክምና ትራንስፎርሜሽንን ለማሳካት ያለመ "የብሔራዊ የኢንጂነሪንግ ሕክምና ኢንቨስትመንት ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር" በአዲስ አበባ በይፋ አስጀምሯል።
ይፋ የተደረገው የዲጂታል ሥርዓት በሀገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን የተሠሩና ወደፊት የሚከናወኑ የጤና መረጃዎችን በአንድ የመረጃ ማዕከል ስር ለማሰባሰብ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
ይህም የተቀናጀና ዘመናዊ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር በማድረግ፣ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ወደ ዲጂታል ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ሲሆን፣ ሥርዓቱ በተለይም ጊዜንና ወጪን በመቆጠብ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ታምኖበታል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት፣ ተበታትነው የሚገኙ የጤና መረጃዎችን ወደ አንድ የተቀናጀ የዲጂታል ሥርዓት ማምጣት እጅግ አስፈላጊ ነው።
ይህም ለዜጎች ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት ከማስቻሉም በላይ፣ ተገልጋዮች የሚገጥሟቸውን እንግልቶች የሚያስቀር መሆኑን ጠቁመዋል።
"ከሐሳብ ወደ ተግባር ለዘላቂ የኢንጂነሪንግ ሕክምና ትራንስፎርሜሽን" በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀው ይህ መርሐ ግብር፣ የዘርፉን ትራንስፎርሜሽን በተግባር ለመተርጎም የሚያስችል መሠረት ይጥላል ተብሏል።
የዲጂታል አገልግሎቱን ተግባራዊ ለማድረግም የተለያዩ ሀገራት ተሞክሮዎች በጥልቀት የተጠኑ ሲሆን፣ የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘቡ ምርምሮች ተካሂደውበታል።
የቴክኖሎጂ ልማት ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታሉ ዓለም እያደረገች ላለው ሰፊ ጉዞ አዲስ በር የሚከፍትና የጤናው ዘርፍ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አካል መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በመሃሪ አለሙ
#ethiopia #ebc #heathsector #healthsystemdigitalization #digitaltransformation

Comments