3 months ago
ሀሴት ሪፍሎክሶሎጂ አዲስ ማዕከሉን በቦሌ አስመረቀ
#ethiopia | በከተማችን ደረጃውን የጠበቀ የሪፍሎክሶሎጂ (የእግርና የእጅ ነርቭ መታሸት) አገልግሎት በመስጠት የሚታወቀው ሀሴት ሪፍሎክሶሎጂ፣ አዲሱንና ዘመናዊ ማዕከሉን በቦሌ ሪያሊቲ ፕላዛ 2ኛ ፎቅ ላይ ዛሬ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ አስመረቀ።
በከፍተኛ የሙያ ስነ-ምግባርና ጥራት የተመሰረተ የሪፍሎክሶሎጂ አገልግሎት።
ተቋሙ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠርና ሙያን በማክበር ረገድ ትልቅ አሻራ እያሳረፈ ይገኛል።
በቦሌ አካባቢ ለሚገኙ ደንበኞች ይበልጥ ምቹና ቅርብ የሆነ አገልግሎት ለማቅረብ የተዘጋጀ።
የተቋሙ መስራችና ባለቤት ወይዘሪት ፅጌረዳ ወልደዮሐንስ በምርቃቱ ወቅት እንደገለጹት፣ ወጣቶች ሙያቸውን አክብረውና በፍቅር በመስራት የሚፈልጉትን ደረጃ መድረስ እንደሚችሉ በተግባር ማሳየት መቻላቸውን ገልጸዋል።
አድራሻ፦ ቦሌ ሪያሊቲ ፕላዛ፣ 2ኛ ፎቅ።
#getu #hassetreflexology #bole #addisababa #healthandwellness #entrepreneurship #ethiopia #newbranch #jobcreation #reflexologyservices #ሀሴትሪፍሎክሶሎጂ #ቦሌ #ጤና #ስራፈጠራ #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago
ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ አዲስ የቴክኖሎጂና የዘመናዊ ስፖርት መፍትሄዎችን አስተዋወቀ
#ethiopia | ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘመናዊ የፒላቴስ ሪፎርመር ስቱዲዮን በመክፈት የአካል ብቃት ዘርፉን ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገሩን አስተዋወቀ።
ተቋሙ ወደ ስራ ያስገባቸው እነዚህ ዘመናዊ የፒላቴስ ማሽኖች ከተለመዱት የጂም መሣሪያዎች የተለየ አሰራር ያላቸው ሲሆን፣ በዋናነትም የሰውነትን ጥንካሬ ለማሳደግ፣ የመተጣጠፍ ብቃትን ለመጨመርና የአካል ሚዛንን ለመጠበቅ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።
የኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ቶማስ ኃይሉ (ቶሚ ኘላስ) በዛሬው እለት ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በሰጠው መግለጫ ማሽኖቹ እንደ ተጠቃሚው አቅም የሚስተካከሉ የመለጠጫ ገመዶችና የሚንሸራተቱ የመለማመጃ ክፍሎች ያሏቸው በመሆኑ፣ ለሆድ ጡንቻ ጥንካሬና ለተስተካከለ የአቋም ለውጥ ውጤታማ መሆናቸው ገልጿል። በተለይም የጀርባ ህመም ያለባቸው ወይም ከጉዳት በማገገም ላይ የሚገኙ ስፖርተኞች እንዲጠቀሙበት የሚመከር አሰራር ነው።
ከዚህ ዘመናዊ ስቱዲዮ በተጨማሪ፣ ወበራ ሶልዩሽንስ ከኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ጋር በመተባበር "ኢትዮ ፊት" የተሰኘ አዲስ የጤናና የአካል ብቃት መተግበሪያን በቅርቡ ለተጠቃሚዎች እንደሚያቀርብ ይፋ ተደርጓል።
ይህ መተግበሪያ ሰዎች ባሉበት ሆነው የቪዲዮ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ፣ እንደ ኢትዮጵያ የምግብ ባህል የተዘጋጀ የአመጋገብ እቅድ እንዲከተሉና የክብደትም ሆነ የልብ ትርታ ለውጣቸውን እንዲከታተሉ ያስችላቸዋል።
መተግበሪያው ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የግል ስልጠናዎችን የሚሰጥ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን ባህላዊ ውዝዋዜዎች ከስፖርት ጋር በማጣመር ለዓለም አቀፍ ተጠቃሚዎች ለማስተዋወቅ ታቅዶ የተዘጋጀ ነው።
የዳንስ ስፖርት በአካላዊና አእምሯዊ ጤና ላይ ስላለው ፋይዳ የሚያሳይ ጥናታዊ ግኝት ይፋ በቅርብ ይፋ የሚደረግ ሲሆን ይህ ጥናት በስፖርታዊ እንቅስቃሴው ውስጥ ዘወትር የሚሳተፉ ግለሰቦች የኃይል መጠናቸው እንደሚጨምር፣ ጭንቀታቸው እንደሚቀንስና ስሜታዊ ሚዛናቸውን እንደሚጠብቁ ተገልጿል።
#ethiodancefitness #pilatesethiopia #ethiofit #healthandwellness #ethiopia #fitnesstechnology #dancefitness #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Comments