7 months ago
"አርሰናሎች ሰዓት በመግደል ጥበብ ተክነዋል!" — ፋብያን ሁርዜለር
#ethiopia | ሁርዜለር ስለ አርሰናል የቆመ ኳስ አጠቃቀምና ስልታዊ የሰዓት ማባከን ድርጊት ያላቸውን ስጋት እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል፦
"አርሰናል እየመራ ባለበት ወቅት የማዕዘን ምት ሲያገኝ ሆን ብሎ ከአንድ ደቂቃ በላይ ይጠቀማል። ብዙ ሰው ልብ ባይለውም፣ ይህ ድርጊታቸው የጨዋታውን ፍሰት በማደናቀፍ ረገድ ትልቅ ሚና አለው። እኔን የሚያሳስበኝም ይሄው ነው!"
አሰልጣኙ በንግግራቸው መሃል አዲስ የህግ ማሻሻያም ጠይቀዋል። እንደ እርሳቸው እምነት ከሆነ፦
* ለእጅ ኳስ ውርወራ፣
* ለማዕዘን ምት እና
* ለቅጣት ምቶች...
የተወሰነ የሰዓት ገደብ የሚጥል ህግ ቢወጣ ለጨዋታው ውበትና ፍሰት ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል።
የአርሰናል "የቆመ ኳስ ስልት" እና ሰዓት የመግደል ብቃቱ (አንዳንዶች Dark Arts እንደሚሉት) ለተጋጣሚ አሰልጣኞች ትልቅ ራስ ምታት መሆኑን የሁርዜለር ትችት ማሳያ ሆኗል። መድፈኞቹ ለዚህ "የሰዓት" ክስ በሜዳ ላይ ምን ምላሽ ይሰጡ ይሆን? የሚጠበቅ ይሆናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #arsenal #brighton #fabianhurzeler #premierleague #footballnews #ethiopia #የእግርኳስዜና

Comments