6 months ago
በክብር ደጃፍ ላይ የሚከፈል ግብር"
(አሸናፊ ማህሌት)
ዘገነርስ ትላንት የታየው ሽንፈት ተራ የእግር ኳስ ውጤት አይደለም፤ ለታላቁ ታሪክ ማድመቂያ የሚከፈል "የመጨረሻ እርከን መስዋዕትነት" እንጂ።
ሰሜን ለንደን ላይ ደስታ የሚመጣው በለቅሶ ታጅቦ ነው። ያቺ በቀላሉ ልትገኝ የሚገባት የኤፌ ካፕ ድል፣ ዛሬ በገዛ እጃችን እንድትፈስ የተደረገችው ለታላቁ የሊግ ክብር ሲባል እንደሆነ ማሰብ "መራርም ቢሆን እውነት" ነው። ህይወት እንዲህ ናት፤ ሁሉንም እቀፋለሁ ስትል ባዶ እጅህን ትቀራለህ። አርሰናል ደግሞ ታላቅነቱን የሚያረጋግጠው ሁሉንም በማግኘት ሳይሆን፣ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን ነገር ለመያዝ ሲል የሚወደውን ነገር አሳልፎ በመስጠት ነው።
"የመድፈኞቹ ቤት ለክብር የሚታጨው፣ በሽንፈት እሳት ተለብልቦ ለበቃው ብቻ ነው።"
በቃ አልቋል አሁን እንገባለን ብለን፣ በሩ ላይ ስንደርስ ዘበኛው "ቁልፉ የለም" እንደሚለን አይነት ስሜት ነው። ነገር ግን ይሄ መራር ሽንፈት የድሉን ድምቀት ይጨምረዋል። ነገ ዋንጫው ሲነሳ፣ ያኔ ትላንት የወደቅንበት ጭቃ ነው የነጩን ማሊያ ውበት ጎልቶ እንዲታይ የሚያደርገው። ትላንት ያጣነው ነገር ነገ ለምናገኘው ክብር እንደ "ማገዶ" ሆኖ ያገለግላል።
መሰዋት ግድ ነው። ሰማዩን ለመንካት ምድሩን መልቀቅ፣ አዲሱን ታሪክ ለመፃፍ የድሮውን ገጽ መቀደድ አለብን። አርሰናልም ትላንት የተሰናበተው ከዋንጫ ሳይሆን፣ ከትናንሽ ግቦች ነው—ለታላቁ ግብ ቦታ ለመልቀቅ!
እና ምድነው "ትልቁን ብርሃን በደማቁ ለማየት፣ አይን በጨለማ መለማመድ አለበት።"
#አርሰናልArsenal #the Gunners
#ትልቁ_ግብ — (The Ultimate Goal)
#north_london Glory #ethioarsenal

Comments