1 month ago
ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ በፒያሳ አዲስ ሾውሩም ከፈተ
♦️ወጣት አዶናይ ብርሃኔ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል
#ethiopia | በኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክስ ንግድ ዘርፍ ውስጥ ከአስር ዓመታት በላይ በታማኝነት እና በጥራት ሲያገለግል የቆየው ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ፣ አሰራሩን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ የሚያሸጋግር ዘመናዊ ሾውሩምን በዛሬው እለት በፒያሳ ከኤሊያና ሆቴል አጠገብ በይፋ አስመረቀ።
ድርጅቱ የምረቃ ስነ-ስርዓቱን ባካሄደበት በዚህ ዕለት በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም በቲክቶክ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆነው ወጣት አዶናይ ብርሃኔ ጋር የነበረውን አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ በማሳደግ የብራንድ አምባሳደርነት ውል ተፈራርሟል።
የድርጅቱን የዕድገት ጉዞና የወደፊት ራዕይ አስመልክተው ንግግር ያደረጉት የፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ ጌጡ፣ ድርጅቱ ከዕለት ዕለት አሰራሩ ባሻገር የቴክኖሎጂ ትራንስፎርሜሽን ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
አቶ ዮሴፍ አክለውም፣ " ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ በዋነኝነት የሚያቀርባቸው ፍሪጆች፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች እንዲሁም አጠቃላይ የቤት ውስጥ ኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ሲሆኑ፣ የምርት አቅርቦቱን በተሻለ መጠን እያሰፋ እና የሸማቹን አቅም ባማከለ መልኩ በጥሩ ዋጋ ምርቱን ለሸማቹ እያቀረበ የሚገኝ ድርጅት ነው" ብለዋል።
ድርጅቱ ከንግድ ስራው ባሻገር በማህበራዊ አገልግሎት፣ የእርዳታ ሰጪ ተቋማትን ድጋፍ በማድረግ ላይ ንቁ ተሳትፎ እንደሚደርግም አብራርተዋል።
አዲሱ ሾውሩም ደንበኞች ምርቶችን በቀላሉ እንዲመለከቱ፣ እንዲያወዳድሩና የተሻለ የግዥ ልምድ እንዲኖራቸው ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
የፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ ማርኬቲንግ ማናጀር አቶ ያሲን አብዱራህማን በስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የዚህን ታላቅ አጋርነት አስፈላጊነት ሲያስረዱ፣ "ከ10 ዓመት በላይ በጥራት፣ በታማኝነት እና በደንበኛ እርካታ ላይ በመመሰረት የሰራነውን ጉዞ ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሸጋገር ይህንን ዘመናዊ ሾውሩም በፒያሳ ከኤሊያና ሆቴል አጠገብ በመክፈታችን ደስተኞች ነን" ብለዋል።
አቶ ያሲን አዶናይ ብርሃኔን ለብራንድ አምባሳደርነት ሲመርጡ በተከተዮቹ ብዛት ሳይሆን ከህዝብ ጋር ባለው ቅርበት፣ በሚፈጥረው አወንታዊ ተፅዕኖ እና ለማህበረሰቡ ባለው ተሳትፎ ምክንያት መሆኑን አብራርተዋል።
ብራንድ አምባሳደር የሆነው ወጣት አዶናይ ብርሃኔ በበኩሉ ከተቋሙ ጋር ለመስራት በመቻሉ የተሰማውን ደስታ ገልጿል። አዶናይ ሲናገር "የፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ አምባሳደር ስለሆንኩኝ በጣም ደስ ብሎኛል። እውነትም ኩራት ይሰማኛል።
በኤሌክትሮኒክስ ደረጃ ኢትዮጵያ ላይ በጣም ታዋቂ ከሆኑ ተቋማት መካከል አንዱ ናቸው። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ህዝብም ተወዳጅ ናቸው። ከስራም በላይ በጎ አድራጎትን የሚያስቀድሙ ስለሆኑ እኔም እነሱን መርጫለሁ" በማለት ተናግሯል።
ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ፤ ከአስር ዓመታት በላይ ያካበተውን ልምድ ከዘመናዊው ዲጂታል አሰራርና ጋር በማስተሳሰር ከቱርክ፣ ከአውሮፓ እና ከቻይና ሀገራት በጥራት የተመረጡ የቤት ውስጥ መገልገያ ምርቶችን በላቀ ደረጃ አስመጥቶ ለኢትዮጵያውያን ሸማቾች በማቅረብ ቀዳሚ ሆኖ እየሰራ ይገኛል።
በጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#popularelectronics #addisababa #elianahotel #piassa #ethiopia #homeappliances #brandambassador #adonaiberhane #tiktokethiopia #techtransformation #newshowroom #shoppingethiopia

Comments